በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት ምክንያት አልባውን የሩሲያን ወረረ አወገዙ


የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን በአርሜንያንስክ ክሬይሚያ ከተማ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ ከፈቀዱ በኋላ የሩስያ ታንክ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ፤ ክሬይሚያ፣ አርሜንያንስክ ክሬይሚያ እእአ የካቲት 24/2022
የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በምስራቃዊ ዩክሬን በአርሜንያንስክ ክሬይሚያ ከተማ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ ከፈቀዱ በኋላ የሩስያ ታንክ በአካባቢው ሲንቀሳቀስ፤ ክሬይሚያ፣ አርሜንያንስክ ክሬይሚያ እእአ የካቲት 24/2022

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ አውጭ የምክር ቤት አባላት የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ሐሙስ ማለዳ ላይ በዩክሬን ላይ ያደረጉትን ወረራ አወገዙ፡፡ የባይደን አስተዳደርም ከ70 ዓመታት በኋላ አውሮፓ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ታይቷል የተባለውን ጦርነት ለማስቆም ፈጣን እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

የህግ መወሰኛው ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ቦምብ ማንዴዝ ዛሬ ባወጡት መግለጫ “ቭላድሚር ፑቲን፣ ሉዓላዊት፣ ነጻና ዲሞክራሲያዊት የሆነች ጎረቤት አገራቸው ዩክሬንን በመፍራት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው፣ ዩክሬናውያንንና ሩሲያውያንን ህይወት መስዋዕት ለማድረግ መወሰናቸውን ታሪክ ያረጋግጣል ብለዋል፡፡

አያይዘውም “ያለምንም ምንም ምክንያት የተነሰነዘረው ይህ ጥቃት የበክሬምሊን ያለውን መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ መነጠል አስፈላጊነት ትልቅ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጎታል፡፡ ዛሬ ዓለም በሞስኮ የሚገኘውን አምባገነን የሚመለከትበት መንገድ እና እንዴት አድርጎ ማስተናገድ እንደሚገባው ታሪካዊ ለውጥ የሚያደርግበት እለት ነው” ብለዋል፡፡

በህግ መወሰኛው ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ከፍተኛ ስልጣን ያላቸው ሪፐብሊካኑ ሴነተር ጂም ሪስክም የሩሲያ ዩክሬንን ከተማዎች መደብደብ “አስቀድሞ የታቀደና ግልጽ የሆነ የጦርነት ድርጊት ነው፡፡ የዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት የተደረገ ቁርጠኝነት ቢኖርም ፑትን ግን የአንድ አገር ሉዓላዊ ድንበር ጥሰዋል” ብለዋል፡፡

ሩሲያ ወታደሮቿን ወደ ዩክሬን ድንበር እያከማችችበት በነበረችበት ባለፉት ሳምንታት የምክር ቤቱ አባላት በሩሲያ ላይ ስለሚጣለው ማዕቀብ ለመስማማር ተቸግረው መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG