በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

14 ከተለያዩ የአለም ማዕዝናት የተመረጡ ሴቶች የብርታት ሽልማት አገኙ


ፋይል ፎቶ - ከተሸላሚዎቹ ሴቶች አንዷ የሆነችው ቻይናዊት ኒ ዩላን (Ni Yulan) ወደ ዋሽንግተን እንዳትመጣ በቻይና መንግስት ታግዳለች
ፋይል ፎቶ - ከተሸላሚዎቹ ሴቶች አንዷ የሆነችው ቻይናዊት ኒ ዩላን (Ni Yulan) ወደ ዋሽንግተን እንዳትመጣ በቻይና መንግስት ታግዳለች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በአለም ማዕዝናት በመልካም ተግባራቸው ልዩ ብርታት ላሳዩ 14 ሴቶች ትላንት ሽልማት ሰጥተዋል። ሽልማቱ የተሰጠው ተሸላሚዎቹ ሴቶች ለፍትህ፣ ለሰብአዊ መብት፣ ለዲሚክራሲ፣ ለጾታ እኩልነትና ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ሳታክቱ ላደረጉት ትግል ነው።

በያዝነው አመት ይህን ሽልማት ካገኙት ሴቶች መካከል ለሴቶች እኩነት የቆመች የሰብአዊ መብት ጉዳይ ጠበቃ ለተገለሉ ዜጎች ተሟጋች የሆነች ያዚዲ ታጋይ፣ አድልዎንና ጽንፈናነትን የሚታገሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች መሪዎች፣ ለዲሞክራሲ የቆመች ሩስያዊት ጋዜጠኛና ሙስናን የምትታገል የኢሚግረሽን ኦፊሰር ይገኙባቸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ያብራራሉ።

“በዚህ አመት የሸለምናቸው ሴቶች በሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ላሳዩት ብርታት እውቅና በመስጠት ነው። በጾታ ላይ የተመሰረተ ሃይል ተጠቃሚነትን ይቃወማሉ ያጋልጣሉም። ሙስናን እየታገሉ በህግ የመገዛት ስርአትን እያጠናከሩ ነው። ለመላ ህዝቦች ፍትህ እንዲኖርና ሰበአዊ መብትም እንዲከበር እየጣሩ ነው።”

ጆን ኬሪ አያይዘውም 14 ቱ ተሸላሚዎች ግልጽ የሆነ መልእክት ያላቸው ተምሳሌቶች ናቸው ብለዋል። ይኸውም ተቀባይነት ማግኘት የማይገባውን ነገር አለመቀበልና ለፍትህና ለመቻቻል መጣር ነው ሲሉ ጆን ኬሩ አስገንዝበዋል።

ከተሸላሚዎቹ ሴቶች አንዷ የሆነችው ቻይናዊት ኒ ዩላን (Ni Yulan) ወደ ዋሽንግተን እንዳትመጣ በሀገርዋ መንግስት ታግዳለች።

ኒሻ አዩብ እንዲህ አይነት ሽልማት ለማግኘት የመጀመርያዋ ትራንስጀንደር ሴት ሆናለች። ትራንስጀንደር ራሳቸውን ከተወለዱበት የጾታ አይነት የተለየ ጾታ ያላቸው አድርገው የሚዩ ሰዎች ናቸው። ኒሻ አዩብ ስለራስዋ የተለየ ሁኔታ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስትናገር ታድያ ሙስሊሞች በሚበዙበት ሀገር የምኖር ትራንስጀንደር ሴት እንደመሆኔ መጠን የምጠይቀው ነገር ቢኖር እንደማንኛውም ዜጋ ተደርጌ እንድታይ ነው ብላለች።

“መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ነው የምንጠይቅ ያለነው። መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶችን፣ የመናገር ነጻነትን፣ ትምህርት የማግኘት ነጻነትንና ሁሉንም መብቶች ለማግኘት ነው የምንጠይቀው።”

በአለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ብርታት ላሳዩ ሲቶች ሽልማት መስጠት ከተጀመረ አስረኛ አመቱን ይዟል። ሽልማቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ (በአስርተ-አመት ውስጥ ማለት ነው) ዩናይትድ ስቴትስ 101 ሴቶችን ላሳዩት ስኬት ሸልማለች።

ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኒክ ቺንግ (Nike Ching) የተቀናበረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ በመጫን ያድምጡ።

14 ከተለያዩ የአለም ማዕዝናት የተመረጡ ሴቶች የብርታት ሽልማት አገኙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG