በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ርዕዮት ዓለሙ ተሸለመች


People wheel a sick man on a makeshift stretcher at the Karaj al-Hajez crossing in Aleppo, Feb. 9, 2014.
People wheel a sick man on a makeshift stretcher at the Karaj al-Hajez crossing in Aleppo, Feb. 9, 2014.

ኢትዮጵያ ውስጥ ወህኒ ቤት የምትገኘውን ጋዜጠኛና አምደኛ ርዕዮት ዓለሙን የዚህ ዓመት ተሸላሚው አድርጎ (IWMF) መርጧታል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:08:50 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


የፍትሕ ጋዜጣ አምደኛና ዘጋቢዋ ርዕዮት ዓለሙ ከሽብር ፈጠራ ቡድን ጋር ተባብረሻል ተብላ ወደ እሥር ከወረደች እነሆ አንድ ዓመት አልፏታል፡፡

በፀረ-ሽብር ሕጉ ክስ ተመሥርቶባት የ14 ዓመት እሥራትና የገንዘብ መቀጫ ፍርድ ከተላለፈባት በኋላ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቀደም ሲል የተላለፈውን ፍርድ አቅልሎ የእሥራቱን ዘመን ወደ አምስት ዓመት አውርዶ የገንዘብ መቀጫውንም ሽሯል፡፡

ርዕዮት ዓለሙ አሁን በዓለምአቀፉ የሴቶች የመገናኛ ብዙኃን ድርጅት - International Women’s Media Foundation – IWMF “በጋዜጠኝነት ለተሠራ ጀብዱ ሽልማት” የዚህ ዓመት /2012/ አሸናፊ ሆና ተመርጣለች፡፡ሥነ-ሥርዓቱ የተካሄደው ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ነው፡፡

የርዕዮት አባት እና የሕግ ጠበቃዋም አቶ ዓለሙ ጌቤቦ ሽልማቱ በጣም እንዳስደሰታቸው ተናግረዋል፡፡

የአምስት ዓመቱ ቅጣት እንዲነሣ ለሰበር ችሎት የቀረበው አቤቱታ ለምርመራ ሊታይ ለፊታችን ማክሰኞ - ጥቅምት ሃያ ተቀጥሯል፡፡

ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ መሠረታዊ የሕግ ግድፈት ፈፅሟል ብለው የሚያምኑት አቶ ዓለሙ ሰበር ሰሚው ችሎት ውሣኔውን ሽሮ ርዕዮትን በነፃ ያሰናብታታል ብለው ያምናሉ፡፡

ሽልማቱን ኒው ዮርክ ተገኝቶ እንዲቀበል ቤተሰቡ ወስኖ የነበረው ዕጮኛዋን ስለሺ ሃጎስን የነበረ ቢሆንም የአሜሪካ ኤምባሲ ቪዛ ስለከለከለው ሳይገኝ ቀርቷል፡፡

ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚደርሱ የተለያዩ ዓይነት ጫናዎች ምክንያት ጋዜጠኛ ሆኖ መሥራት ከባድ መሆኑን የተናገረው ስለሺ ሰዎች “ማንበብ እንኳ በሚፈሩባት ሃገር ውስጥ ፎቶግራፏን እያወጣች ስትዘግብ የቆየችውና በሥራዋ ምክንያትም ለእሥር የተዳረገችው ርዕዮት ዓለሙ ይህ በጋዜጠኝነት ለተሠራ ጀብዱ የተሰጣት ሽልማት የሚገባት ነው” ብሏል፡፡ እራሱም ጋዜጠኛ መሆኑን የገለፀው ስለሺ አክሎም “ይህ ሽልማት በየትም ሥፍራ እንደርዕዮት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሁሉ ብቻቸውን እንዳልሆኑ፤ የሚታዘቡና የሚያዩ እንዳሉም መልዕክት የሚያስላልፍ ነው” ብሏል፡፡

ቀደም ሲልም በሽልማቱ ሥነ-ሥርዓት ላይ ወክላት እንድትገኝ ርዕዮት እራሷ ፈልጋ የነበረው ወ/ት ብርትኳን ሚደቅሣን የነበረ ቢሆንም በፕሮግራም አለመጣጣምና አለመስተካካል ችግር ምክንያት ሳትገኝ ቀርታለች፡፡
ርዕዮት ዓለሙ
ርዕዮት ዓለሙ

ወ/ት ብርትኳን ለቪኦኤ በሰጠችው መግለጫ “ይህ ሽልማት ስሙ እንደሚያመለክተው በሙያው ላይ ደፋር ሰው የሚያገኘው ሽልማት በመሆኑ እንደርዕዮት ዓይነት ለሙያው ታማኝ የሆነ ሰው መሸለም ያለበት፣ በእሥር ላይ ላለች ሴት ሁኔታዎች ከባድ በመሆናቸው ብርቱ ብትሆንም ይበልጥ የሚያበረታም ነው” ብላ “ይገባታል” ያለችውን የጀብዱ ሽልማት ላገኘችው ለርዕዮት ደስታዋን ገልፃለች፡፡

ርዕዮትን ወክሎ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኘው የፀሐይ አሣታሚ መሥራችና ኃላፊ አቶ ኤልያስ ወንድሙ ነው፡፡

የዛሬውን ሽልማት ከርዕዮት ጋር ያሸነፉት የጋዛዋ አስማ አል ጉልና የአዘርባይጃኗ ከድጃ ኢስማይለቫ ሲሆኑ በዕድሜ ዘመን የስኬት አገልግሎት ደግሞ ፓኪስታናዊዋ ጋዜጠኛ ዙቤይዳ ሙስጠፋ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG