ዋሽንግተን ዲሲ —
የኢትዮጵያ ሴቶች የመብት ማዕከል (Center for the Rights of Ethiopian Women/CREW)ከአራት ዓመታት በላይ በእሥር ለቆየችውና ከጥቂት ወራት በፊት ለተለቀቀችው ጋዜጠኛ ርእዮት ዓለሙ እሑድ ኅዳር 26 ቀን 2008 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ የክብር ምሳ ግብዣ አደረገላት፡፡
በዚህ የግብዣ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታማኝ በየነ፣ሶሊያና ሽመልስ እና እህቷ እስከዳር ዓለሙ ተገኝተው ስለ ርእዮት ዓለሙ የሚያውቁትን በግብዣ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ለተገኘው ታዳሚው አካፍለዋል፡፡ ጋዜጠኛ ርእዮት ዓለሙም ከእስር ከተፈታች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕዝብ ፊት ንግግር አድርጋለች፡፡
ጋዜጠኛ ርእዮት ዓለሙ እሥር ቤተ በነበረችበት ወቅት በጡት ሕመም ስትሰቃይ እንደነበር፤ ይህም ለካንሰር ሕመም ሊያጋልጣት ይችላል የሚል ስጋት በቤተሰቦቿ በኩል ተፈጥሮ እንደነበር ፤የሚታወቅ ሲኾን "አሁን ከካንሠር ነፃ ነኝ" ስትል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች፡፡
ቆንጂት ታየ ያዘጋጀችውን ዘገባ ለማዳመጥ የተያያዘውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።