በኢትዮጵያ በተከሰተው አስከፊ ድርቅ ምክንያት ወደ 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ይፈልጋል። ከእነዚህ ውስጥም ሕፃናት በከፍተኛ ሁኔታ በምግብ እጥረት ተጠቅተዋል።
በሪቲ ሃዋስ ትባላለች የሦስት ዓመት ልጇ በምግብ እጥረት በመጎዳቱ ታሞ ሆስፒታል ተኝቷል።"ምንም የሚበላ ምግብ ስለሌለን ልጄ ታሞብኛል።” ትላለች የሦስት ዓመት ልጇን እንደታቀፈች።
ልጆች ትምሕርት ቤት መሄድ አቁመዋል። እቤት ውስጥ ቁጭ ብለው በድርቁ ምክንያት ከብቶቻቸው ያለቁባቸው ቤተሰቦቻቸውን ይረዳሉ። የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይ ከድርቁ ጋር በተያያዘ ለረሃብ የተጋለጡትን ሕፃናት ለመታደግ ረደኤት ከሚሰጡ ድርጅቶች ጋር እየሠራ መሆኑን ይናገራል።
የሕፃናት መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት ሠራተኛ ሳሙኤል ተፈራ ሕፃናቱ በምግብ እጥረት ምክንያት ለበሽታ እንደሚጋለጡ ይነገራል።
"የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና ረሃብ በሚከሰትበት ጊዜ የሕፃናቱ የአዕምሮ ዕድገት ይቀንሳል። የማሰብ ብቃታቸው ዝቅተኛ ይሆናል እንዲሁም ለበሽታ ይጋለጣሉ።” ይላል ሳሙኤል ተፈራ።
እስካሁን ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ተገኝቷል። ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግሥትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 1.4 ሚሊዮን ዶላር ለዚህ ዓመት ያስፈልጋል ብለዋል። ይህ ገንዘብ የሚያስፈልገውም ምግብ ለማቅረብ እንደሆነ ታውቋል።
"በድርቁ ምክንያት መንግስት ከሚሰጠን ርዳታ ውጪ ምንም የሚላስና የሚቀመስ ነገር አጥተናል። በቤታችን ውስጥ ምንም የለም። ልጆቻችንን የምናበላው ምንም ነገር የለንም፡፡ የምንጠጣው ውሃም የለንም”
የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ማርታ ቫን ደርዎልፍ በድርቁ ምክንያት የተጎዱና አሁን በሚሰጣቸው ሰብአዊ ርዳታ የሚተዳደሩ ሰዎች የሚኖሩበት መተሐራ አካባቢ ተዘዋውራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋልች።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።