ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላንና ከኦሮሚያ ከተሞች ዐዋጅ ጋር ተያይዞ ኦሮሚያ ውስጥ በተነሣው ተቃውሞና ግጭት የበርካታ ሰው ሕይወት መጥፋቱና ከ3,500 ሰው በላይ መታሠሩን ኦ.ፌ.ኮ አስታወቀ፡፡ ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባም መታሠራቸው ታውቋል፡፡
ከአራት ዓመታት የእሥር ቆይታ በኋላ፤ የእሥር ጊዜያቸውን ጨርሰው ከአምስት ወራት በፊት የተፈቱት የቀድሞ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ዕለት ታሠሩ፡፡
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ፤ ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት፣ በፓርቲያቸው አመራር አባላት፣ በታዛቢዎቻቸው፣ በደጋፊዎቻቸውና ሕገ መንግሥቱን አክብረው መብታቸውን ሲጠይቁ በነበሩት ላይ ሁሉ ከፍተኛ የእሥር ዘመቻ እየተካሄደ እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
በተያያዘ ሦስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት በኦሮሞ ዜጎች ላይ በየጊዜው የሚደርሰው ማንገላታት፣ስደት፣ሞት እና እሥራት አሳሳቢ መኾኑን ጠቅሰው ፤አሜሪካ በጉዳዩ ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ውይይት እንድታደርግና ሕጋዊ ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል፡፡
ዘገባውን የሠራችው ጽዮን ግርማ ነች፡፡
ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡