ዋሺንግተን ዲሲ —
ፎቶ - ፋይል
Embed
share
Embed
share
The code has been copied to your clipboard.
The URL has been copied to your clipboard
No media source currently available
ቀጥተኛ መገናኛ
በኦሮሚያ ክልል አሰላ ከተማ፣ በጉጂ ዞን፣ በሃርቀሎ ወረዳና በሆሮ ጉዱሩ፤ በወለጋ ኢበንቱ ወረዳ ተማሪዎችና ነዋሪዎች ድብደባ እየተፈፀመባቸውና በመከላከያ አባላት እየታሠሩ መሆናቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
አንድ የአሰላ ከተማ ነዋሪ ባለፉት አምስት ቀናት ውስጥ የአንደኛ፣ የሁለተኛና የመሰናዶ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ሠላማዊ ሠልፍ ወጥተው የአዲስ አበባን የአካባቢዋን ከተሞች የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላንና ኦሮሚያ ውስጥ ይካሄዳል ያሉትን እሥራትና ግድያ መቃወማቸውን ገልፀዋል፡፡
አንዲት የአንደኛ ደረጃ ተማሪ ከሰልፉ ወቅት ስትሮጥ ሽቦ ላይ ወድቃ የአንድ ዐይኗን ብርሃን ለማጣት መዳረጓን የከተማይቱ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
አንድ የከተማይቱ ነዋሪ ደግሞ ሆዷ ላይ በዱላ ተመትታ በብርቱ መጎዳቷን አመልክተው ትምህርት ተቋርጦ ከተማይቱ በጦር እየተጠበቀች ነው ብለዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡