በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የግል ከፍተኛ የትምህር ተቋማት ማህበር ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ያወጣዉን መመሪያ ተቃወመ!


የኢትዮጵያ ትምህት ሚኒስቴር ያወጣዉ መመሪያ የግል ከፍተኛ ተቋማት የህግና የመምህርነት ትምህርት እንዳይሰጡ ያግዳል። በአገሪቱ የርቀት ትምህርትም እንዲቆም አድርጓል።

የህዝብ ግንኙን ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ምክንያቱን ሲያብራሩ፣ እርምጃዉ የትምህርት ጥራት ለማስጠበቅ ነዉ ብለዋል። ሁሉም ባይባሉ አብዛኞች የግል ከፍተኛ የትምህት ተቋማት የትምህርት ሚኒስቴርን ግብአት አያሙዋሉም፣ ለቴክኒክና ሙያ የተቀመጡ መስፈርቶች ስራ ላይ አያዉሉም ብለዋል።

የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበር ስራ አስኪያጅ ዶክተር ነጋ ናማጋ በበኩላቸዉ፣ በኢትዮጵያ የትምህርት ጥራት መዉደቁን አምነዉ፣ አንድ በቅርቡ የተካሄደ አንድ ጥናት፣ ለትምህርት ጥራት መጉዋደል አንዳንድ የመንግስት ተቋማትንም ሃላፊ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል።

ይልቁንስ ጥራታቸዉን የጠበቁ ተብለዉ አምስት ከፍተኛ የግል ተቋማት በጥናቱ መለየታቸዉን ተናግረዉ መመሪያዉ ተቋማቱን በጅምላ መፈረጁን ተቃዉመዋል።

መመሪያዉ የወጣዉ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ለመስከረም ትምህርት ጅማሮ ዝግጅት በሚደረግበት ጊዜና ሳይታሰብ በድንገት በመሆኑም ባለሃብቱና የአገሪቱ ትምህርት ስርአት ላይ ጉዳት ያስከትላል ብለዋል። ከመሆኑም በድንገት ሰለወጣ ለግል ተቋማት ጉዳት እንደሚያስከትል የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አበራ አባተ፣ የከፍተኛ ትምህርት አቅርቦት በአገሪቱ ክልሎች ሁሉ ከመቸዉም ጊዜ የተስፋፉና፣ እርምጃዉ ወደፊትም ስለሚቀጥል ጥራት የጎደለዉ ትምህርት በግል ተቋማት መሰጠቱ አስፈላጊ አይደለም ብለዋል። የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ማህበር ስራ አስኪያጅ ዶክተር ነጋ ናማጋ ግን የመንግስት የትምህርት ተቋማት ብቻ

ለሰማኒያ ሚሊዮን ህዝብ ትምህርትን ያዳርሳሉ ብሎ መገመት አይቻልም ብለዋል። ሁለቱ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያዎች ለኢትዮጵያ ትምህርት ጥራት መዉደቅ መፍትሔ ያሉትን ጥቁመዋል። ዉይይታቸዉን አዳምጡ።

XS
SM
MD
LG