በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ የበረራ ደህንነት ባለሙያዎች የኢትዮጵያ የአየር አደጋ ግኝቶችን ተቃወሙ


ቦይንግ 737 ማክስ በዋሽንግተን
ቦይንግ 737 ማክስ በዋሽንግተን

የዩናይትድ ስቴትስ የአየር ደህንነት ባለሙያዎች በቦይንግ 737-ማክስ አውሮፕላን መከስከስ ጋር ተያይዞ፤ ሁለት ቁልፍ የኢትዮጵያ ምርመራ ግኝቶችን ተቃውመዋል።

የበረራ ቁጥር 302 መጋቢት 2011 ከአዲስ አበባ እንደተነሳ ብዙም ሳይቆይ ተከስክሶ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ 157 ሰዎች ሙሉ ለሙሉ ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ ወይም ኤን.ቲ.ኤስ.ቢ የኢትዮጵያ የዓየር ተቆጣጣሪዎች በሪፖርታቸው ለሰራተኞች ስልጠና እና ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ ሂደቶች በቂ ትኩረት አልሰጡም ብሏል።

ለረጂም ጊዜ የዘገየ ሪፖርቱን ዓርብ ታኅሣሥ 21/ 2015 ዓ.ም. ያወጣው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ምርመራ ቢሮ፤ ለአደጋው መንስዔ የቦይንግ ጠቋሚ መሳሪያዎች የሚያስተላልፉትን እና መረጃን የማይቀበል ስርዓትን በምክንያትነት አስቀምጧል።

ሪፖርቱ ጠቋሚዎቹ በሚቀበሉት የተሳሳተ መረጃ ምክንያትም የአውሮፕላኑ አፍንጫ በተደጋጋሚ እንዲያዘቀዝቅ ማድረጉን ገልጾ ምንም እንኳን አብራሪዎቹ በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢደርሳቸውም አውሮፕላኑን መቆጣጠር አለመቻላቸውን ገልጿል።

ይሁን እንጂ ኤን.ቲ.ኤስ.ቢ ጠቋሚ መሳሪያው ሊሳሳት የቻለው አውሮፕላኑ ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ወፍ ገብቶበት ተጎድቶ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል። ይህ አባባል በኢትዮጵያ መርማሪዎች ችላ ተብሏል።

ኤን.ቲ.ኤስ.ቢም የኢትዮጵያውያን አቻዎቻቸውን በንድፍ ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር የሰራተኞቻቸው ስልጠና እና የአደጋ ምላሽን ቸል ብለዋል ብሏል።

የአውሮፕላኑ አባላት በነባሩ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ህግ እና ደረጃዎች መሰረት ለበረራ ፍቃድ ያላቸውን እና ብቁ መሆናቸውን የኢትዮጵያ መርማሪዎች ሪፖርት አረጋግጧል። ሪፖርቱ አክሎም ይሁን እንጂ የበራራ አባላቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የአውሮፕላኑ "አደናጋሪ ማስጠንቀቂያዎች" መደናገጣቸውን በመግለጽ የአውሮፕላኑን ንድፍ ለአደጋው ተጠያቂ አድርጓል።

በበረራ ቁጥር 302 ላይ የደረሰው አደጋ ከአምስት ወራት በፊት ይኸው የአውሮፕላን ሞዴል በኢንዶኔዥያ ተከስክሶ የ189 ሰዎች ህይወት ማለፉ የሚታወስ ነው።

እነዚህ ተከታታይ አደጋዎች በአውሮፕላኑ ውስጥ ያለውን ችግር ያጋለጡ ሲሆን ሞዴሉ በዓለም ዙሪያ ከአገልግሎት ታግዶ እንዲቆይ ተደርጓል። ይህን ተከትሎም ቦይንግ 20 ቢሊየን ዶላር ወጪ አውጥቷል። ለአውሮፕላኑ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ አሰጣጥ ጋር ከነበሩ የሂደት ጉድለቶች ጋር ተያይዞም የፍርድ ቤት ክስ እንዲመሰረትበት ተደርጓል።

አውሮፕላኑ ስራ ካቆመ ከ20 ወራት በኋላ በድጋሚ ስራ የጀመረ ሲሆን ኢትዮጵያ 737-MAX አውሮፕላን ወደ አገልግሎት ከተመለሰባቸው የመጨረሻዎቹ አገሮች ተርታ ተሰልፋለች።

XS
SM
MD
LG