በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቦይንግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ አደጋ ከሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ጋር ሥምምነት ላይ ደረሰ


The Boeing logo
The Boeing logo

የዩናይትድ ስቴትሱ ቦይንግ ኩባኒያ መጋቢት 1/2011 ዓ.ም ቀን ወደኬንያ በረራ ላይ እንዳለ በወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ ጄት አደጋ ህይወታቸውን ካጡት 157 መንገደኞችና የበረራ ሠራተኞች ቤተሰቦች ጋር ሥምምነት ላይ መድረሱን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘገበ።

ቦይንግ አውሮፕላኑ ከአብራሪዎቹ ቁጥጥር ውጪ ሆኖ እንዲወድቅ ያበቃው ምክንያት የሶፍትዌሩ ችግር መሆኑን እና 737 ማክስ ጄቶቹ ለበረራ ደህንነት ብቁ እንዳልነበሩ ማመኑን ኢሊኖይ ክፍለ ግዛት ቺካጎ ከተማ ፍርድ ቤት የገቡ ሰነዶች መረጃ ጠቅሶ አሶሽዬትድ ፕሬስ አመልክቷል።

በኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን ላይ የደረሰው አደጋ በቦይንግ ማክስ ጀት ላይ የደረሰ ሁለተኛ አደጋ ሲሆን ከኢትዮጵያው አደጋ በኋል ማክስ ጀቶች ከበረራ ታግደው ቆይተው የበረራ ፈቃድ ያገኙት በዚህ የአውሮፓ 2021 ዓመት መሆኑ ይታወሳል።

ቦይንግ ትናንት ረቡዕ ያደረገው ሥምምነት በአደጋው ህይወታቸውን ላጡት ሰዎች ቤተሰቦች የሚከፈል ካሳ አይጨምርም፥ ቢሆንም የሟቾች ቤተሰቦች በየሀገራቸው ሳይሆን በዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች በኩል በየግላቸው ካሳ እንዲጠይቁ የሚፈቅድ መሆኑ ታውቋል።

XS
SM
MD
LG