በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አደጋ ሰለባዎችና ቤተሰቦች ካሳ ጉዳይ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትሱ ቦይንግ ኩባንያ ኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዥያ ውስጥ ለደረሱት የበርካታ ሰው ህይወት የጠፋባቸው አውሮፕላን አደጋዎች ለተጎዱ ሰዎች እና ማኅበረሰቦች መርጃ የሚውል አንድ መቶ ሚሊዮን ዶላር መመደቡን ከአንድ ሳምንት በፊት አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ አደጋ ሰለባዎች ቤተሰቦችና የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት የወደቀበት አካባቢ አርሶ አደሮች ግን፣ ስለገንዘቡ ምንም የሰማነው ነገር የለም ማለታቸው ሮይተርስ ዘግቧል።

ገንዘቡን የመደበው በአደጋዎቹ ሰለባዎች ቤተሰቦች በተመሰረቱት ክሶች ምክንያት አለመሆኑን ያስታወቀው ቦይንግ፣ ገንዘቡን ለሀገሮቹ መንግሥታት አትራፊ ላልሆኑ ድርጅቶች እንደሚያስረክብ መግለፁን ዘገባው አመልክቷል።

ይሁን እንጂ የገንዘብ ዕርዳታው ለማን እንደሚገባ፣ ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ እስካሁን ግልፅ አይደለም።

የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን የወደቀበት ስፍራ አካባቢ፣ አርሶ አደሮች መሬታችን የአውሮፕላኑ ስብርባሪ የተበተነበት በመሆኑና በመታጠሩ፣ ሌላ ቦታ ሄደን ለመከራየት አቅም የለንም ብለዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG