ሃያ ስምንት አፍሪካውያን ሴት ፍልሰተኞች ትላንት ከሊብያ እሥር ቤት ሲፈቱ የአሥራ ሁለት ዓመት ዕድሜ ህፃናትም ይገኙበታል፡፡
ኢትዮጵያን በይፋ በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ኤርትራን በመጨመር አንድ የኢኮኖሚ ማኅበረሠብ ለመፍጠር መስራት አለባቸው አሉ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሽብር ፈጠራንና ፅንፈኛ የሁከት ቡደኖችን ለማሸነፍ ግብፅ ለምታደርገው ጥረት አስተዳደራቸው ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ አስታውቀዋል፡፡
በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተው ድርቅ ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች በገደለባት ሶማሌላንድ መንግሥቱ የልማት ሥራዎችን አቁሞ የገንዘብና አስተዳድራዊ ትኩረቱን ህይወት በማዳን ሥራ ላይ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የምግብ ዋስትናን በዓለም ዙሪያ ማረጋገጥ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅም ጉዳይ መሆኑ ላለፉት ሁለት ቀናት መጋቢት 20 እና መጋቢት 21 / 2009 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲሲ ላይ በተካሄደው ዓመታዊው የዓለም የምግብ ዋስትና ጉባዔ ላይ ተገልጿል፡፡
ጆአኪም ደመር ይባላል። ስዊድናዊ የዶክሜንትሪ ወይም የዘጋቢ ፊልም ሠሪ ነው።
የአፍሪካ የበሽታዎች መከላከያ ማዕከል (Africa CDC) የአምስት ዓመት ዕቅዱን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትናንት ይፋ ያደረጉት የ“አሜሪካ ትቅደም” በጀት በሃገር ውስጥም፣ በሃገር ውስጥም ከሃገር ውጭም እያነጋገረ ነው፡፡ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወታደራዊ ኃይላቸውንና የደኅንነት ክንፋቸውን፣ በተለይ የሕግ አስከባሪውን ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ ማጠናከር ነው ሃሣባቸው፡፡
ኮንፌዴሬሽን የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመት በዓል በአዲስ አበባ እያከበረ ነው፡፡ በነገው ዕለት በሚያካሂደው ሠላሳ ዘጠነኛው ጉባዔም ፕሬዚዳንት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ይመርጣል፡፡ ሃያ ዘጠኝ ዓመታት በፕሬዚዳንትነት የቆዩት ካሜሮናዊው ኢሣ ሃያቱ ዘንድሮ ጠንከር ያለ ፉክክር ገጥሟቸዋል::
“ቆሼ” እየተባለ በልማድ የሚጠራው አካባቢ ነዋሪዎች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸውን በሰሞኑ አደጋ ያጡ ኀዘንተኞች የቀሩትን ዜጎች ለመታደግ የሚወሰደው እርምጃ አፋጣኝ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡ “በሥጋት ውጭ እያደረን ነው” ብለዋል ነዋሪዎቹ፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ከእርሣቸው የቀደሙት ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ “በምርጫው ወቅት ኒው ዮርክ በሚገኘው ሕንፃዬ ላይ የስልክ መሥመሮቼን ጠልፈው ይሰልሉኝ ነበር” ሲሉ ላሰሙት ክሥ ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥት ማስረጃ እንዲያቀርብ ግፊቱ አሁንም እንደበረታ ነው፡፡
አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ “ቆሼ ሠፈር” እየተባለ በሚጠራው ቆሻሻ ማስወገጃ ሥፍራ ህይወታቸው ያለፈ ዜጎች ቁጥር 80 ደርሷል፡፡
ኢሕአዴግና ሃያ አንድ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በቅድመ ድርድር ነጥቦች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት ዛሬ ቀጥለዋል፡፡ በድርድሩ በሚሳተፉት ፓርቲዎች አወካከልና በአደራዳሪዎች አመራረጥ ላይ ዛሬ የተወያዩት ተሳታፊዎቹ፣ የመጨረሻ እልባት ለመስጠት ለፊታችን ቅዳሜ ሣምንት ሌላ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ኮንግሬስ ያሉ ሪፖብሊካውያን ባለፉት ሰባት ዓመታት ቃል በገቡት መሠረት ኦባማ ኬር እየተባለ የሚጠራውን የጤና ጥበቃ ሕግ ሠርዘው በሌላ እንዲተኩ ውጥረት ውስጥ ገብተዋል። ባለፈው አስተዳደር የወጣው ሕግ ቀድሞ የጤና መድኅን ያልነበራቸው ብዙ አሜሪካውያን በተመጣጣኝ ዋጋ የጤና ጥበቃ አገልግሎት ማግኘት ያስችላቸዋል።
ዛሬ እአአ መጋቢት ስምንት በየዓመቱ የዓለማቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም ዙሪያ ይከበራል፡፡‘A Day without Women’ “ሴት አልባ ውሎ” የሚል መጠሪያ በሱጡት በዛሬው ዓድማቸው ቀኑ ከሥራ ቀርተው ቤት መዋል ነው፡፡
ሴሽንስ ባለፍው ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት ሲያገለግሉና የዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ፣ በከፍተኛ አማካሪነት ሲሰሩ በነበረበት ወቅት ከሩሲያው አምባሳደር ጋር ሁለት ጊዜ ባደረጓቸው ግንኙነቶች ዙሪያ የተነሱ ውዝግቦችን ተከትሎ ነው፤ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በፍትሕ ሚኒስትሩ ያላቸውን “ሙሉ” እምነት የገለፁ ሲሆን፤ የኮንግረሱ ዴሞክራቶች ሴሽ ንስ ከሥራቸው መልቀቅ አለባቸው እያሉ ነው።
ዓለምቀፍ የዱር አራዊት ቀን - ማርች 3 ቀን 2017
በሚመጡት ጥቂት አሥርት ዓመታት ውስጥ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ከእንስሳት የሚገኙ የምግብ ተዋፅዕዎች ተፈላጊነት ከዛሬው አኳያ እስከ አራት እጥፍ እንደሚያድግ ተነገረ፡፡ በሚመጡት ጥቂት አሥርት ዓመታት ውስጥ በአንዳንድ የአፍሪካ ሀገሮች ከእንስሳት የሚገኙ የምግብ ተዋፅዕዎች ተፈላጊነት ከዛሬው አኳያ እስከ አራት እጥፍ እንደሚያድግ ተነገረ፡፡
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በመጤዎች ጥላች ላይ የተመሠረተው ኃይል ተጠቃሚነት አገርሽቷል። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በመዲናይቱ ፕሪቶርያ በውጭ ተወላጆች ሱቆች ላይ ጥቃት እየተፈፀም ነው። የቁጣው መነሻ ጥልቅና ውስብስብ መሆኑ እየተገለፀ ነው፡፡
“በሰላምም ይሁን በአመፅ - ነፃነት በአስፈላጊው መንገድ ሁሉ!” ይል ነበር ማልኮም ኤክስ በየንግግሩ አዝማች፤ እንደልማድም ሆኖበት፤ ደግሞም የነፃነትን አስፈላጊነት ለማፅናት፡፡ ጥቁሩ የመብቶች ተሟጋችና ታጋይ ማልኮም ኤክስ ልክ የዛሬ 52 ዓመት፤ (በኢትዮጵያ የጊዜ አቆጣጠር) የካቲት 14/1957 ዓ.ም ኒው ዮርክ ከተማ ላይ ንግግር እያደረገ ሳለ በተተኮሰበት ጥይት በሰላሣ ዘጠኝ ዓመት ዕድሜው መገባደጃ አካባቢ ተገደለ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ