በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የፍትሕ ሚኒስትር ጄፍ ሴሽንስ የሩሲያ መንግሥት በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ ገብነት ፈፅሞ ከሆነ ከሚደረገው ምርመራ ራሳቸውን አገለሉ


ሴሽንስ ባለፍው ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ሴኔት ሲያገለግሉና የዶናልድ ትራምፕ የምረጡኝ ዘመቻ ላይ፣ በከፍተኛ አማካሪነት ሲሰሩ በነበረበት ወቅት ከሩሲያው አምባሳደር ጋር ሁለት ጊዜ ባደረጓቸው ግንኙነቶች ዙሪያ የተነሱ ውዝግቦችን ተከትሎ ነው፤ ከዚህ ውሳኔ የደረሱት። ፕሬዚዳንት ትራምፕ በፍትሕ ሚኒስትሩ ያላቸውን “ሙሉ” እምነት የገለፁ ሲሆን፤ የኮንግረሱ ዴሞክራቶች ሴሽ ንስ ከሥራቸው መልቀቅ አለባቸው እያሉ ነው።

XS
SM
MD
LG