የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ወዳጁ የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በመንበረ ፀባዎት ቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ሰኞ ሊፈፀም የነበረው የፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት የቀብር ሥነ ስርዓት ወደ ዛሬ ማክሰኞ የተላለፈው ከቤተሰብ በቀረበ ጥያቄ እንጂ ሌላ በምንም ምክንያት አለመሆኑን የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ለመደራደር ቅድመ-ውይይት በማድረግ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት በመስፈርቶችና የድርድር ነጥቦች ዙሪያ ቀዳሚ ውይይቶች ተካሂደዋል። ለመሆኑ ኢህአዴግ ከበርካታ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሲወያይ በተለይ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ ምርጫዎች ከፍተኛ ድጋፍን የሚይገኘው የኦሮሞ ፌዴራሊስ ፓርቲ በምን አይነት ሁኔታ ላይ ይገኛል?
"ጆን ብራውን በጣም የተበሳጨ አሜሪካዊ ነው፡፡ ባርነት የማስወገጃው ብቸኛ መንገድ ተቋሙን በአምፅ ማሰወገድ ነው ብሎ ያምን ነበር፡፡ በጦርነት መደምሰስ"የሀርፐርስ መሪ ብሔራዊ ፓርክ ዋና የታሪክ ተመራማሪው ዴኒስ ፍራይ የባርነት መሪና ተቃዋሚው ጆን ብራውንና ጓዶቹ ያንን የአሜሪካ የፅልመት ዕድሜ ለማብቃት የጀመሩትን ትግል ያስታውሳሉ፡፡
የዓመቱ ምርጥ አልበም፤ የዓመቱ ምርጥ ቀረፃ፤ የዓመቱ ምርጥ ዘፈን! በእግር ኳስ ቋንቋ ቢሆን ኖሮ ‘ሃት ትሪክ’ ይባል ነበር - በአንድ ጨዋታ በአንድ አግቢ ለሚቆጠሩ ሦስት ተከታታይ ጎሎች! በታላቁ የሙዚቃ ዓለም ፍልሚያ መድረክ፣ በግራሚው ግጥሚያ ግን “ትራይፌክታ” ይባላል።
የኬንያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዓለም እጅግ ግዙፍ የሚባለው የስደተኞች መጠለያ ሠፈር እንዳይዘጋ ማገዱን የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅቶች አሞግሰዋል። መንግሥት ከሦስት መቶ ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ያስጠለለውን ዳዳብ የሚባለውን መጠለያ ሰፈር እንደሚዘጋ አስታውቆ ነበር። አብዛኞቹ በሠፈሩ ውስጥ የተጠለሉት ስደተኞች ከሶማሊያ የገቡ ሲሆኑ መንግሥቱ ሊዘጋው የወሰነው ለሀገሪቱ ፀጥታ አደጋ ይደቅናል በሚል እንደነበረ ገልጿል።