የዑጋንዳ ዋናው የተቃዋሚ መሪ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ

የዑጋንዳ ተቃዋሚዎች በፓሊስ ሊገደቡ አልቻሉም

እማኞች እንዳሉት የዴሞክራሲያዊ ለውጥ መድረክ የሚባለው ቤሲጄ የሚመሩትን ተቃዋሚ ድርጅት ሌሎችም የአመራር አባላት ፖሊስ ይዞ መውሰዱን እማኞች ተናግረዋል።

የዑጋንዳ ዋናው የተቃዋሚ መሪ ኪዛ ቤሲጄ በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ቤሲጄ ዛሬ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላለፉት ሠላሣ ዓመታት ሥልጣን የኖሩትን ዮዌሪ ሙሴቬኒን በርቀት ተከትለው ሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ማምሻውን እየወጡ ያሉ የድምፅ ቆጠራ ውጤቶች እያመለከቱ ነው።

እማኞች እንዳሉት የዴሞክራሲያዊ ለውጥ መድረክ የሚባለው ቤሲጄ የሚመሩትን ተቃዋሚ ድርጅት ሌሎችም የአመራር አባላት ፖሊስ ይዞ መውሰዱን እማኞች ተናግረዋል።

የፓርቲው አባላት ገዥው ፓርቲ ድምፅ እጭበርብሯል ብለው ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት እየተዘጋጁ ሳሉ ፖሊስ በተሰበሰቡበት ሕንፃ ላይ አስለቃሽ ጋዝ መርጨቱ ተገልጿል።

ሌላው ተፎካካሪ የሆኑት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ምባባዚ ዛሬ በፖሊስ ታጅበው ተወስደዋል።

በአፍሪካ ሥልጣን ላይ በመቆየት አቻ የሌላቸው ሙሴቬኒ በዛሬው ምርጫ ቀድመው በወጡ የቆጠራ ውጤቶች 62 ከመቶውን ይዘው እየመሩ ሲሆን ቤሲጄ በ32 ከመቶ ድምፅ ሁለተኛ ናቸው። ምባባዚ ከሁለት ከመቶ ያነሰ ድምፅ ይዘው በርቀት ሦስተኛነት እየተከተሉ እንደሆኑ ታውቋል።

በተጨማሪም፣ ቤሲጄ በመታሠራቸው ውጥረቱን ከፍ አድርጎታል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች በዋና ከተማዋ ካምፓላ ድንጋይ ሲወረውሩና መንገዶችን ሲዘጉ፥ ፖሊስ ደግሞ ሁኔታውን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጋዝ ሲተኩስ ታይቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ቤሲጄ ፕሬዘዳንት ይዌሪ ሙሰቪኒን በሁለተኛነት እየተከተሉ መሆናቸውን በከፊል የወጡ የምርጫ ውጤቶች ይጠቁማሉ።

ሊዛቤት ፖላት ከካምፓላ ዘግባለች። ሰሎሞን ክፍሌ ያጠናቀረውን ።

Your browser doesn’t support HTML5

የዑጋንዳ ዋናው የተቃዋሚ መሪ በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ዋሉ