በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩጋንዳ ቤሲጂዬ እንደገና ታሠሩ


የዩጋንዳ ባንዲራ

የዩጋንዳው የተቃውሞ መሪ ኪዛ ቤሲጂዬ በዋስ በተለቀቁ በሃያ አራት ሰዓታት በአንድ ወር ውስጥ ለአራተኛ ጊዜ ተይዘው ታስተዋል፡፡

ቤሲጊዬን የፀጥታ ኃይሎች ይዘው ዛሬ ያሰሯቸው ወደ ዋና ከተማይቱ ካምፓላ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እያሽከረከሩ ሳሉ ነው፡፡

በሥፍራው ተቀርፆ የነበረ ቪድዮ ፖሊሶቹ የቤሲጂዬን መኪና መስኮት በኃይል ይደበድቡና ወደ እርሣቸውም አስለቃሽ ጋዝ እየረጩባቸው እንደነበረ ያሣያል፡፡

ቤሲጂዬ በዋስ ተለቅቀው የነበረው በሕገወጥ መንገድ በተጠራ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል ተብለው ለሰባት ቀናት ከታሠሩ በኋላ ነበር፡፡

ቤሲጂዬ ተቃውሟቸውን ከጀመሩ ካለፉ ሦስት ሣምንታት ወዲህ እየተያዙ እየተለቀቁ ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ መታሠራቸው ነው፡፡ የእርሣቸው የፓርቲ ባልደረባ ሮበርት ማዖ ከካምፓላ 64 ኪሎሜትሮች ወጣ ብሎ በሚገኘው የናካሶንጎላ ወህኒ አሁንም እንደታሠሩ ነው፡፡

ኪዛ ቤሲጂዬ ባለፈው ሣምንት ከተያዙ በኋላ የወጣ ቪዲዮ እጃቸውን ይዞ በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ለማሣፈር የነበረን ግብግብ ያሣያል፡፡ ዛሬ ማለዳም እንዲሁ ከመኪናቸው ውስጥ ለማስወጣት ፖሊስ የተጠቀመበትን የኃይል እርምጃ የሚያሣይ ቪዲዮ ወጥቷል፡፡

መኪናቸውን መስበርን፣ ጋዝ መኪናቸው ውስጥ መርጨትን የመሣሰሉ፡፡

ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG