የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው፣ የሦርያውን ቀውስ በማርገብ እረገድ ቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ወሳኝነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የሦርያው ፕሬዚደንት ባሽር አል-አሳድ የአገራቸውን የአምስት ዓመታት የርስ በራስ ጦርነት ለማቆም ይቻል ዘንድ በጠላትነት ላለመተያየት የተደረሰው ስምምነት፣ ተስፋ የሚፈነጥቅ ነው ሲሉ ዛሬ ማክሰኞ መናገራቸው ተሰማ።
ስምምነቱ ሥራ ላይ እንዲውል መንግሥታቸው የበኩሉን እንደሚያደርግ ፕሬዚደንት አሳድ ከጀርመን ቴሌቪዥን ጋር ባካሄዱት ቃለ-ምልልስ ተናግረዋል።
የዩናይትድ ስቴትሱ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው፣ የሦርያውን ቀውስ በማርገብ እረገድ ቀጣዮቹ ጥቂት ቀናት ወሳኝነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
ውጩ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ ይህን የተናገሩት ትናንት ሰኞ ዋሽንግተን ውስጥ ለጋዜተኞች በሰጡት ቃል ነው።
እርሳቸውና የሩስያው አቻቸው ሰርጌ ላህሮቭ፣ ስምምነቱ ይፋ ከሆነበት ካለፈው ቅዳሜ ወዲህ ተደጋጋሚ ጥሰቶች መታየታቸውን አመልክተው፣ ይሁንና ለጥሰቱ ይፋ የሆነ እውቅና ወይም ህጋዊነት መስጠት እንደማይፈልጉ ጠቅሰዋል።
Your browser doesn’t support HTML5