በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ወደሶሪያ ወታደሮች ባስችኩዋይ ልትልክ የጸረ ኣይሲስ ህብረት ልዩ ልዑኩ ተናገሩ


የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ ብረት ብግሩክ (Brett Mcgurk) ከየዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry) ጋር
የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ ብረት ብግሩክ (Brett Mcgurk) ከየዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚስተር ጆን ኬሪ ( John Kerry) ጋር

አሜሪካ ወደሶሪያ ወታደሮች ባስችኩዋይ ልትልክ የጸረ ኣይሲስ ህብረት ልዩ ልዑኩ ተናገሩ።

በዓለም ኣቀፉ ጸረ ኣይስሲ ህብረት የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ ልዑክ ብረት ብግሩክ (Brett Mcgurk) ለCBS ቴለቭዢን Face The Nation ፕሮግራም በሰጡት ቃለ መጠይቅ ዓለም ኦቀፉ ጸረ አይሲስ ሕብረት ባለፉት ሳምንታት በቡድኑ ይዞታ የነበሩ ኣካባቢዎችን ተቆጣጥረዋል፡ ብዛት ያላቸው ተዋጊዎቹንም ገድለዋል ማለታቸውን የኣሜሪካ ድምጹ Victor Beattie ባጠናቀረው ዘገባ ጠቅሱዋል።

ጉዳዩ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ ልዩ ሃይሎቹ በህ ቀን ይዘምታሉ የለው ዝርዝርዝ ወስጥ ኣልገባም ያሉት የዩናይትድ ስቴትሱ ልዩ ልዑክ ቁጥራቸው ወደ ሃምሳ የሚጠጉት የልዩ ኦፐሬሽን ሃይሎች ባፋጣኝ ሰሜን ሶሪያ ይገባሉ ብለዋል። በቅርቡ እንደተገለጠውም የዘመቻቸው ዓላማ ኣይሲስን በመውጋት ላይ ላሉት የአረብ ሃገሮች ሃይሎች ስልጠና ምክርና እገዛ ለመስጠት መሆኑን አመልክተው የሚደርሰው የአረብ ሃገሮቹ ሃይሎች ከፍተኛ ስኬት እያስመዘገቡ ባሉበት በዚህ ወቅት ነው ብለዋል።

“ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ኣንድ ሺህ ኣንድ መቶ ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ግዛት ኣስለቅቀው ተቆጣጥረዋል። ወደሶስት መቶ የሚጠጉ የአይሲል ተዋጊዎችን ገድለዋል። አብዛኛው አሸባሪ የሚፈለፈልበትን የRaqaaን የአይሲልን መዲና ከሌላ ኣካባቢ እንዳይገናኝ መነጠል ላይ ያተኮረ ዘመቻ ነው። “

ግቡም ኣሉ የያዛቸውን ግዛቶች ማስለቀቅ:፡ መሪዎቹ እያሳደዱ መግደል፡ የገንዘብ ምንጫቸውን መቁረጥ ባዕዳን ተዋጊ የሚመለምሉበት ዓለም ኣቀፍ መረብ መሰባበር መሆኑ ንየዩናይትድ ስቴቱስ ልዩ ልኡክ ኣስረድተዋል ። የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት አሸባሪው ቡድኑ ቱኒዥያ ቱርክ ቤይሩት እና ፓሪስ ውስጥ ያደረሳቸውን ጥቃቶችና በግብጽ ሲናይ የሩስያ የመንገደኞችን ኣውሮፕላን የጣለው ቡድን በዓለም ኣቀፍ ሰላምና ጸጥታ ካሁን ቀደም ከደረሱት ሁሉ የከፋ ስጋት ደቅኑዋል ሲል ባለፈው ዓርብ ያሳለፈው ን ውሳኔ ልዩ ልዑኩ ጠቅሰዋል ።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ በምስራቅ እስያ ሃገሮች መሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደማሌዢያ ጉዞ ከመጀመራቸው ኣስቀድሞ በሰጡት ቃል በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራው ህብረት አይሲልን ይደመስሰዋል ሲሉ ዝተዋል።

“በስፍራው ካሉ የኣካባቢው ኣጋሮቻችን ጋር ሆነን በሁሉም ግንባሮች ስትራተጂያችንን አጠናክረናል። በኛ አይሲል ደህንነታችን ላይ ኣደጋ እንዳይደቅን እዚያው ኢራቅና ሶሪያ ውስጥ ቡድኑን ማጥቃታችንን መሪዎቹን እና ኣዛዦቻቸውን ማጥፋታችንን እንቀጥላለን ። ይሄን ኣሸባሪ ቡድን እንደመስሰዋለን”

በዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የስለላ ኮሚቴ አንጋፋ ዲሞክራት ኣባል Diane Feinestein በበኩላቸው ለCBS ቴሌቪዢን Face The Nation program በሰጡት ቃል የኦባማ ኣስተዳደር የሚከተለው ጎዳና በቂ ኣይደለም ብለዋል።

“የኔ ስጋት ጊዜ የለንም ፡ የዓመታት ጊዜ የለንም ። ኣሁኑኑ ማፋፋም ነው ያለብን፡ ምክንያቱም ISIL እንደመንግሥት ያህል ሆንዋል። ሰላሳ ሺህ ተዋጊ አለው፡ ሲቪላዊ መሰረተ ልማቱን ይዙዋል፡ ገንዘብ ኣለው፡ ወደሌሎች ሃገሮች እየተስፋፋ ነው። ስለዚህ እጅግ በጣም ከባድ ነው። እንደሚመስለኝ በሌሎች ኣካባቢዎች ከማን ኣንሼ በሚል ፉክክር የጀመሩ ሊሎች የአሸባሪ ድርጅቶች ኣሉ። የኣይሲል ግን ከነዚያ ለየት ይላል። እጅግ በጣም ጠንካራ ነው፡ መጋፈጥ ያመብንም በጣም ጠንካራ በሆነ መንገድ ነው ።”

ወደሰሜን ሶሪያ ጥቂት ሃይሎች መላኩ መፍትሄ ስለማይሆን ሰፋ ያለ የልዩ ሃይል ሰራዊት መላክ ኣለብን ሲሉ ሴነተር ፋይነስታይን አሳስበዋል። የጸረ ኣይሲሱ ህብረት ልዩ ልዑክ ግን አሜሪካ መራሹ ህብረት ነውጠኛውን ቡድን ለመደምሰስ በገባው ቃል ዝግ ኣላለም በማለት ተሙዋግተዋል።

“ባለፈው ዓመት እንቅስቃሴኣችንን ለማፋፋም የሚያስፈልጉ ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል። ለምሳሌ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ ኣይሲል በራካ እና በኢራቅ ሞሱል መካከል የነበረውን ዋና የአቅርቦት ማጉዋጉዋዣ መስመር ለመቁረጥ ከኩርዶችና ከአረብ ሃይሎች ጋር ሆነ ኢራቅም ሶሪያም ውስጥ ባንድ ጊዜ ጥቃት ኣካሂደናል። በጣም የተዋጡ ዘመቻዎች ነበሩ። ወደ ሰሜን ሶሪያ የሚዘምተው ልዩ ሃይላችንም ተልእኮው በመሬቱ ላይ ያለው ሃይል ሰፋ ብሎ ተደራጅቶ ወደራካ እንዲገሰግስ ማድረግ ነው። ያን ከስድስት ወር በፊት ልናደርገው ኣንችልም ነበር። ኣሁን ሁኔታው ተመቻችቱዋል።

የምንከተለው ስልት አሉ የዩናይይትድ ስቴትሱ ልዑክ ኣይሲልን ከቱርክ ጋር የሚያገናኘውን ከራካ ወደሞሱል መግቢያውን መስመር ቆርጠን እዚያው ያለበት ኢራቅና ሶሪያ ውስጥ ማነቅ ነው። የኢራቅ ሃይሎች የሰሜኑዋን ኣንባር ከተማ እንዲነጥቁት እንደርጋለን ። ከውጭ ተዋጊ እየመለመለ የሚያስገባበትን ዓለም ኣቀፍ መረብ ለመቆራረጥ ጠንካራ ኣለም ኣቀፍ ትብብር ለመመስረት ዕቅድ መኖሩን ኣብራርተዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

አሜሪካ ወደሶሪያ ወታደሮች ባስችኩዋይ ልትልክ የጸረ ኣይሲስ ህብረት ልዩ ልዑኩ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:54 0:00

XS
SM
MD
LG