ሰሜናዊ ካሜሩን የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች አጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች ማድረሳቸው ተገለጸ

  • ቆንጂት ታየ

ባመንዳ፣ ካሜሩን፣ እኑጉ እና ናይጄርያ

አራት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አምስት ሰዎች መግደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ የከተማዋ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሰሜናዊ ካሜሩን የቦኮ ሃራም ተዋጊዎች አዘውትረው የጥቃት ዒላማ በሚያደርጉዋት ከተማ አጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃቶች መድረሳቸው ተገለጸ።

ቦዶ በተባለች ከተማ ዛሬ ሰኞ ማለዳ አራት አጥፍቶ ጠፊዎች ቦምብ አፈንድተው ቢያንስ ሃያ አምስት ሰዎች መግደላቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል አንድ የከተማዋ ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሁለቱ አጥፍቶ ጠፊዎች ትልቁ የከተማዋ ዋና ገበያ ሌሎቹ ሁለቱ ደግሞ የከተማዋ ዋናው ኬላ ላይ ማፈንዳታቸውን ዜናው አመልክቷል።

ለጥቃቱ ሃላፊነት የወሰደ ወገን የለም። ሆኖም በአካባቢው በተደጋጋሚ ጥቃቶችን ያደረሰው ቦኮ ሃራም ተጠርጥሯል።