የሶማልያ ማዕከላዊ መንግሥት፣ ጎሣን መሠረት አድርጎ መሪዎችን የመምረጡን አሠራር አስወግዶ አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው ሂደት ለመተካት ተስማምተዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የሶማልያ ማዕከላዊ መንግሥት እና በከፊል ነፃ የሆነችው የፑንትላንድ ግዛት ባለሥልጣናት፥ ከዘንድሮው ምርጫ በኋላ፥ ጎሣን መሠረት አድርጎ መሪዎችን የመምረጡን አሠራር አስወግደው፥ አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው ሂደት ለመተካት ተስማምተዋል።
እርምጃው በሶማልያ ለዓመታት የቆየውን የፖለቲካ አለመረጋጋትና ግጭቶች ሊያስወግድ የሚያስችል አንድ እጅግ ጠቃሚ እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል።
ሞሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰን አጭር ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5