አገራቸው በሶሪያ የምታካሂደውን የዓየር ድብደባ “በዚያች አገር ያሉ ያሏቸው አሸባሪዎች እስኪደመሰሱ ድረስ አታቆምም፤” ሲሉ የሩሲያው የውጭ ጉዳይሚንስትር ሰርጌይ ላቫሮቭ (Sergei Lavrov) ተናገሩ።
የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር አስተያየት የተሰማው ለአምስት ዓመታት ለዘለቀው የሶሪያ ጦርነት እልባት ለማበጀት ታልሞ በጀኔቫ የሚካሄደውና በቋፍላይ የሚገኘው የሰላም ድርድር፤ የሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች፤ የሶሪያ መንግስትና የአማጽያኑ ተጠሪዎች አንዳቸውም የዛሬውን ሦሥተኛ ቀን ከአደራዳሪው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ (Staffan de Mistura) ተገናኝተው ሳይነጋገሩ ካሳለፉ በኋላ ነው።
ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያለውን አሸባሪ ቡድን ጃብሃት አል-ኑስራን (Jabhat al-Nusra) የዓየር ድብደባው ኢላማ ነው ያሉት ላቭሮቭ፤ አገራቸው እያካሄደች ያለችውን የዓየር ድብደባ ለምን እንደሚገባት እንደልታያቸው አመልክተዋል።
የምታካሂደው የዓየር ድብደባ ከአሸባሪዎች ይልቅ በፕሬዝዳንት ባሽር አላሳድ ተቃዋሚዎች ላይ የተነጣጠረ ነው፤ በሚል በምዕራባውያን ክፉኛ ብትተችም ሩሲያ በበኩሏ ግን ስታስተባብል መቆየቷ ይታወሳል።
በሶሪያ የሚካሄደውን የዓየር ድብደባ እንዲቆም በትላንትናው ዕለት ጥሪ ያቀረቡት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ (John Kerry) የተኩስአቁሙም ስምምነት በአስቸኳይ ተፈጻሚ መሆን አለበት፤ ብለዋል። ጆን ኬሪ በሶርያ ላይ ያደረጉትን ንግግር ከዚህ በታች ካለው ቪድዮ ይመልከቱ።
Your browser doesn’t support HTML5