ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል

ከመስመጥ ከተርፉት ውስጥ ከግራ ወደ ቀኝ እስማኤል ሞውሊድ ከሶማሊያ ከቀኝ ወደ ግራ ሙሐዝ መሐመድ ከኢትዮጵያ በአቴንስ ግሪክ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ

ሚስትና ልጁን ያጣ፣እናትና ወንድሞቹን ውሃ የበላበት፣እህቱን እና 28 ጓደኞቹን ያጣ ናቸው። ስላሳለፉት ጉዞ አስቸጋሪነትና ለመሄድ ስለተዘጋጁ ስደተኖች የሚነግረን ወጣትም ከግብጽ አነጋግረናል።

ባለፈው ሳምንት ማብቂያ በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኤጀንሲ እማኞችን አነጋግሮ በሰጠው መግለጫ ገልጿል።

ከዚህ አደጋ የተረፉት 41 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ሃይል ተርፈው ወደ ግሪክ ተሻግረው ነበር። የአውሮፓ ህብረትና የግሪክ መንግስት በአሁኑ ሰዓት ስደተኞችና ፍልሰተኞች በመበራከታቸው፤ ወደየሃገራቸው እንዲመለሱ ማዘዣ እየሰጡ ነው።ሶሪያዊያንም ወደ ቱርክ ወደሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ሲመለሱ ቆይተዋል።

ጽዮን ግርማ ከጀልባ አደጋ በህይወት ተርፈው ግሪክ ከገቡ መካከል ጥቂዎቹን አነጋግራለች።

በግብጽ ባህር ዳርቻ በዚህ ሳምንት በባህር ውስጥ 500 ሰዎች ህወታቸውን ባጡ ማግስት፤ ለጉዞ የተዘጋጁ በርካታ ኢትዮጵያዊያን፣ ሶማሊያዊያን፣ ኤርትራዊያንና ሌሎችም ናቸው። ጽዮን ግርማ ግብጽ የሚገኘውን ቢራ ገመዲን አነጋግራም አያይዛ ዘግባለች።

Your browser doesn’t support HTML5

ከመስመጥ የተርፉት ኢትዮጵያውያን 11 ብቻ ናቸው፤ ሦስቱን አነጋግረናቸዋል

Your browser doesn’t support HTML5

በሜዲትራንያን ባህር ላይ ጀልባ ተገልብጦ 500 ስደተኞች ሰጥመው ሕይወታቸው ማለፉን የተ. መ. ድ. ከእማኞች ባገኘው መግለጫ አስታወቀ