በዓለም ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አሽቆልቁሏል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ “አፋኞች” ተብለዋል

በዓለም ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አሽቆልቁሏል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ “አፋኞች” ተብለዋል በዛሬውለት ይፋ በሆነ ዓመታዊ ጥናት። በዋሽንግተን ዲሲ መሰረቱን ያደረገው የመብት ተሟጋች ቡድን ፍሪደም ሀውስ በዓለም ዙሪያ ከሰባት ሰዎች መካከል ስድስቱ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ባልተጠበቀባቸውና የጋዜጠኞች ደህንነት ዋስትና በሌለባቸው ሀገሮች ይኖራሉ።

በዓለም ዙሪያ ላለፉት 12 ዓመታት የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ያለማቋረጥ ማሽቆልቆሉን ነው በዛሬውለት በዋሽንግተን ዲሲ ይፋ የሆነው የፍሪደም ሀውስ ጥናት ይፋ ያደረገው። የፍሪደም ሃውሷ ጄኔፈር ደነም ምክንያቶቹን ሲያስረዱ፣ "በጋዜጠኞች ላይ በተለያዩ ሁኔታዎች ሳቢያ የሚደርሱ ጥቃቶች በዓለም ዙሪያ መጠናከራቸው አንዱ ምክንያት ነው። አምባገነን መንግስታትና ጽንፈኞች ነጻና ገለልተኛ የመገናኛ ብዙሃን ላይ አፈናና ወከባ ያከናውናሉ። የተደራጁ ወሮበሎች፣ በሙስና የተዘፈቁ ባለስልጣናት፣ የመሬት ልማት ባለስልጣናት፣ የሃይማኖት አክራሪዎችና የልዖላዊነት ጥያቄ ለጋዜጠኞች ስራ እጅግ አስፈሪ ርእሶች ናቸው።" ብለዋል።

ከጊዜ ወደ ጊዜ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ማሽቆልቆል ከሚታይባቸው ሀገሮች መካከል ኤርትራና ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆኑ ቆይተዋል። እንዲያውም ሁለቱ ሀገሮች በጋዜጠኞች ይዞታ ክፋት የሚፎካከሩ ነው የሚመስሉት። ጄኔፈር ደናም፣ "ከዚህ ቀደም ጋዜጠኞች በነጻነት እንዲሰሩ የሚያስችል ድባብ ተፈጥሮ ነበር። በአሁኑ ወቅት ቁልፍ የተባሉ ጋዜጠኞችና አዘጋጆች ታስረዋል፣ አንዳንዶቹ እንዲያውም ለብዙ አመታት ታስረው ይገኛሉ። የነጻ የመገናኛ ብዙሃንን መብት የሚጠብቅና የሚያከብር ሕግ በወረቀት ቢኖርም፣ በተግባር ላይ ሲውል አይታይም።፡ ይላሉ።

የፍሪደም ሃውስ አርማ

ኤርትራ በአፍሪካም ሆነ በዓለም የከፋ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት ይዞታ የሚታይባት ሀገር እንደሆነች የፍሪደም ሃውስ ጥናት ይጠቁማል።

"ኤርትራውያን ጋዜጠኞች እራሳቸው ያለ ግድብ ዘገባዎችን በነጻ ያለ ምንም ፍርሃት እስከሚሰሩ ድረስ ነጻ የመገናኛ ብዙሃን መገናኛ በአገሪቷ አለ ማለት አይቻልም።" ብለዋል።

በኒውዮር መሰረቱን አድርጎ ለጋዜጠኞች መብት የሚታገለው ቡድን CPJ በዚህ ሳምንት ባወጣው የመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይ ቅድመ ምርመራ ከሚያከናውኑ ሀገሮች መዝገብ ላይ የመጀመሪያዋ ኤርትራ ስትሆን፣ ሰሜን ኮርያ እና ሳዑዲ አረብያ ሁለተኛና ሦስተኛ ተብለዋል። ኢትዮጵያ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተጠቅሳለች።

ኮርትኒ ራዴክ የCPJ የመብት ሞጋች ቡድን ኋላፊ ናቸው። የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች በቅድመ-ምርመራ ሰንጠረዥ ላይ ግንባር ቀደም የሆኑባቸውን ምክንያቶች ሲገልጹ፣ "ከአፍሪካ አገሮች ሁሉ በግንባር ቀደም ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ስማቸው ሊጠቀስ የበቃበት ምክኒያት ብዙ ጋዜጠኞችን በማሰራቸው ነው። የኢንተርኔት ገደብ በማስፈራቸውንና፣ ነፃ የመገናና ብዙሃን ባለመኖራቸውም ጭምር ነው። እንዲያውም የመገናኛ ብዙሃን የሉም ቢባል ይሻላል። ኤርትራ በጣም ዝቅተኛ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ስርጭት አላት ብለናል። በነዚህ ምክንያቶች ነው ቀዳሚዎቹ አገሮች የሆኑት።" ብለዋል።

መደበኛ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ስርጭቶችን ማለትም የቴሌቭዥንና ሬድዮ ሞገዶችን በማፈን የሚታወቁ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ መንግስታት፤ በድረ-ገጽም ጭምር የስለላ መርጃዎችን በመልቀቅ ይታወቃሉ ሲሉ የአፈናውን መጠን የሚያስረዱት የሂውማን ራይትስ ወች መረጃ አጠናቃሪ ፌሊክስ ሆርን ናቸው።

"እነዚህ መሳሪያዎች መንግሥት በሰዎች ኮምፒውተር ላይ፣ በስካይፕ ንግግራቸው ላይ፣ ምን እንደሚሰሩና በኮምፒውተራቸው ላይ ባለው ቪድዮም ሰዎች ምን እያደርጉ እንዳሉም ማየት ይቻላል። ስለዚህ እነዚህ የድረገጽ ህዋሶች በጣም ኃይለኛ የስለላ መሳራያዎች ናቸው።" ብለዋል።

በዛሬውለት ፍሪደም ሀውስ ባወጣው ዘገባ የመገናኛ ብዙሃን መብትን የሚጥሱ ሀገሮች፤ በራሳቸው ህገ-መንግስትና በፈረሟቸው ዓለም አቀፋዊ ድንጋጌዎች ሊዳኙና፤ ተግባራዊ ሊያደርጉ ይገባቸዋል ሲል፤ መንግስታት ለነጻነት ስምምነቶቹ ተገዥ እንዲሆኑ ጥሪ አስተላልፏል።

የመገናኛ ብዙሃን ስራዎች ላይ ቅድመ-ምርመራ በማካሄድ ኤርትርና ኢትዮጵያ በማያስመሰግነው የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ቡድን CPJ መዝገብ ላይ ቀዳሚ ሆነዋል።

ሔኖክ ሰማእግዜርና ሳሌም ሰለሞን ያጠናቀሩት ዘገባ ዝርዝሩን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በዓለም ዙሪያ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት አሽቆልቁሏል፤ ኢትዮጵያና ኤርትራ “አፋኞች” ተብለዋል

ኤርትራና ኢትዮጵያ በማያስመሰግነው የጋዜጠኞች ቅድመ-ምርመራ ሰንጠርዥ ቀዳሚ ሆኑ

የጋዜጠኞች ተሟጋች ቡድኑ ባወጣው በቅድመ ምርመራ መዝገብ ላይ የመጀመሪያዋ ኤርትራ ስትሆን፣ ሰሜን ኮርያ እና ሳዑዲ አረብያ ሁለተኛና ሦስተኛ ተብለዋል። ኢትዮጵያ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ላይ ተጠቅሳለች።

የጋዜጠኞች ተሟጋች ቡድኑ ከዚህ ቀደም በሚያወጣቸው የተለያዩ ዘገባዎችና የማያስመስግኑ የመገናኛ ብዙሃን ደረጃ ሰንጠረዦች፤ ኤርትራና ኢትዮጵያ እንዲሁም ሶማሊያ በግንባር ቀደምነት ሲጠቀሱ ቆይተዋል። በኢትዮጵያና ኤርትራ በአጠቃላይ ጋዜጠኞችና ጸሃፊዎችን በማሰር ከአፍሪካ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ዝርዝሩን ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

ኤርትራና ኢትዮጵያ በማያስመሰግነው የጋዜጠኞች ቅድመ-ምርመራ ሰንጠርዥ ቀዳሚ ሆኑ