በኦሮሚያ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ቀጥሏል

በኦሮሚያ በምዕራብ አርሲ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች መንገድ ዘግተው

በኦሮሚያ በምዕራብ አርሲ ለተቃውሞ የወጡ ሰዎች መንገድ ዘግተው

በአምቦ እስር ቤት ተቃጥሏል፤አንድ የዘጠኝ ዓመት አዳጊ ተገድሏል

በአዲስ አበባና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ልማት ማስተር ፕላን ዕቅድ ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በኋላ እንደገና ያገረሸው ተቃውሞ ከሦስት ወር በላይ አስቆጥሯል፡፡

በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በምዕራብ አርሲ፣ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ፣ በጋራ ሙለታ ግራዋ ወረዳ ዛሬም የተቃውሞ እንቅስቃሴ እንደነበር፤ ዛሬ በአምቦ የአዋሮ አንደኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው አንድ የዘጠኝ ዓመት ልጅ በጥይት መገደሉን የዐይን እማኝ መሆናችውን የገለጹ ምንጮች ተናግረዋል።

በተጨማሪም እዚያው አምቦ ውስጥ የሚገኝ ማረሚያ ቤት ላይ ቃጠሎ መነሣቱን፣ በተጨማሪም ምዕራብ አርሲ ውስጥ በሻሸመኔ ወረዳ አጄ በተባለች የገጠር ከተማ ውስጥ የሚገኝ እሥር ቤት ተሰብሮ እሥረኞች እንዲወጡ መደረጉን የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ዘግበዋል፡፡

ዛሬ የደረሱንን ሪፖርቶች ጽዮን ግርማ እንደሚከተለው አቀናብራ አዘጋጅታዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በኦሮሚያ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ቀጥሏል