በግብጽ የምሽት ክበብ በደረሰ ጥቃት አስራ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል

  • ቆንጂት ታየ

ግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ ውስጥ በሚገኝ የምሽት ክበብ ዛሬ ዓርብ ሌሊት በደረሰ ሞሎቶቭ ኮክቴል (Molotov cocktail)በሚባለው ቤት ውስጥ የሚሰራ ፈንጂ ጥቃት ቢያንስ አስራ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።

አጉዛ በሚባለው የካይሮ ኣካካባቢ በሚገኘው ኤል ሳያድ ምግብ መጠጥ ቤት የደረሰው ጥቃት ምክንያት ምን እንደሆነ አልታወቀም።

የግብጽ የጸጥታ ባለስልጣናት ጥቃቱ ከሽብርተኝነት ጋር የተቆራኘ አይደለም በማለት እያስተባበሉ ቢሆንም አንዱ ከሌላው የሚጋጩ መግለጫዎች እየሰጡ ናቸው።

የግብጽ የአገር አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ድንገቱ የጀመረው በምሽት ክበቡ ሰራተኞችና በሌሎች ሰዎች መካከል ጸብ ከተነሳ በሁዋላ ሰዎች ክበቡ መግቢያ በር ላይ ቦምቡን አፈነዱት ብለዋል። ዘገባውን ከተያያዘው የምድጽ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በግብጽ የምሽት ክበብ በደረሰ ጥቃት አስራ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል