በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአብዱልፋታህ ኤል-ሲሲና የኃይለማርያም ደሣለኝ መግለጫ


የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በብሔራዊ ቤተመንግሥት - አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2007 ዓ.ም
የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በብሔራዊ ቤተመንግሥት - አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2007 ዓ.ም

ግብፅ ወደ እንዲህ ዓይነቱ የትብብር መንፈስ ፊቷን ያዞረችው ከዚህ ቀደም ለዘመናት ስትከተለው የቆየችው መንገድ ከእንግዲህ እንደማያስኬድ መሪዎቿ በመገንዘባቸው ነው ሲሉ አንድ ኢትዮጵያዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ለቪኦኤ በሰጡት ትንተና አመልክተዋል፡፡

አባይ
አባይ

please wait

No media source currently available

0:00 0:05:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ኢትዮጵያ ውስጥ ይፋ መንግሥታዊ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የግብፅ ፕሬዚዳንት አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ የሃገሮቻቸውን ግንኙነት፣ አካባቢያዊና አህጉራዊ የፀጥታ ጉዳዮችን በተመለከተ ጠቅለል ያሉ ጉዳዮችን እንዲሁም የኅዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ መወያየታቸውን ለጋዜጠኞች አስታውቀዋል፡፡

መሪዎቹ በአዲስ አበባው ብሔራዊ ቤተመንግሥት ዛሬ /ማክሰኞ፤ መጋቢት 15/2007ዓ.ም/ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የያዙት አቅጣጫ ትክክለኛ ነው ብለው እንደሚያምኑና ትናንት ኻርቱም ላይ የተፈራረሙት ሠነድም ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኅዳሴ ግድብ ማሣያ
የኅዳሴ ግድብ ማሣያ

“…የታላቁን ኅዳሴ ግድብ በተመለከተ ወንድም ከሆነው ከሱዳን ሕዝብ ጭምር ትናንት ኻርቱም ላይ የተፈራረምነው የመርኅ ስምምነት በሦስቱ ሃገሮች መካከል ስለሚኖር የጠነከረ ግንኙነት በትክክለኛ አቅጣጫ የተደረገ እርምጃን እንደሚያመለክት እናምናለን…” ብለዋል የግብፁ ፕሬዚዳንት፡፡

የኢትዮጵያው ኃይለማርያም ደሣለኝም “…ያሣካው ዋናው እርምጃ በሁለታችንም በኩል የታየው ፖለቲካዊ ፍቃደኝነትና ቁርጠኝነት ነው፤ ይህ ደግሞ ለሁለቱም ሕዝቦቻችን ጥቅም ስንል እና በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ትሥሥር ለማጠናከር ያደረግነው ነው…” ብለዋል፡፡

አቤል አባተ - የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ
አቤል አባተ - የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ

በሌላ በኩል ደግሞ ግብፅ ወደ እንዲህ ዓይነቱ የትብብር መንፈስ ፊቷን ያዞረችው ከዚህ ቀደም ለዘመናት ስትከተለው የቆየችው መንገድ ከእንግዲህ እንደማያስኬድ መሪዎቿ በመገንዘባቸው ነው ሲሉ አንድ ኢትዮጵያዊ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ተመራማሪ ለቪኦኤ በሰጡት ትንተና አመልክተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዙትን የድምፅ ፋይሎች ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG