በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኅዳሴ ግድብ ግንባታ ዓለምአቀፍ አማካሪ ተመረጠ


የሕዳሴን ግድብ እንዲያጠኑ ሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መመረጣቸውን ትላንትናና ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ የተቀመጡ የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ተወካዮች ገልፀዋል።

please wait

No media source currently available

0:00 0:04:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የሕዳሴን ግድብ እንዲያጠኑ ሁለት ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች መመረጣቸውን ትላንትናና ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ የተቀመጡ የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን ተወካዮች ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር አቶ ዓለማየሁ ተገኑ ከስብሰባው በኋላ ለቪኦኤ እንደገለፁት አንደኛው በአብይነት ወይም በዋነኛነት ሁለተኛው ደግሞ በተከታይነት መመረጣቸውን ገልፀዋል፡፡

ምንም እንኳ ሚኒስትሩ ኩባንያዎቹ ደብዳቤዎች ተልከውላቸው መልስ እስኪሰጡ ድረስ ማንነታቸውን እንደማይገልፁ ቢናገሩም አንድ ለመንግሥት ቅርበት ያለው የኢትዮጵያ ዜና አውታር ግን “… በዋና ኩባንያነት የተመረጠው “በኢትዮጵያ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ በመሣተፍ ልምድ ያለው ቢአርኤል ኢንጂነሪንግ፤ በተከታይ አማካሪነት ደግሞ ከሞዴሊንግ ጋር የተያያዙ ከፊል ሥራዎችን እንዲያከናውን ግብፅ ያቀረበችው ዴልታ የሚባል ኩባንያ መመረጡን…” ዘግቧል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG