የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች፥ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሁለት ሣምንታት በፊት የመኪና መተላለፊያ መንገድ ዘግታችሁ ነበር ተብለው የታሠሩ 11 ተማሪዎች ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።
አዲስ አበባ እና ዋሽንግተን ዲሲ —
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ አመራር አባላት አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች፥ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።
በዚህ ላይ መለስካቸው አምሃ ከአዲስ አበባ የላከው ሪፖርት አለ። አስቀድመን እናቀርባለን።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ለተቃውሞ ሰልፍ በወጡበት ወቅት የተነሳ ፎቶ [ፋይል - ሮይተርስ]
በሌላ በኩል ደግሞ፥ ከትላንት በስቲያ ረቡዕ መጋቢት 7 ቀን 2008 ዓ.ም. በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሆነችው በሰበታ ከተማ የኦሮሞ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት /OPDO/ የከተማይቱን ሁለተኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ስብሰባ ከጠራ በሁዋላ የፌዴራል ኃይል ተጠርቶ ተደበደብን ይላሉ ተማሪዎች።
ከሁለት ሣምንታት በፊት የመኪና መተላለፊያ መንገድ ዘግታችሁ ነበር ተብለው የታሠሩ 11 ተማሪዎች ደግሞ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። የአፋን ኦሮሞ አገልግሎት ባልደረባ ጃለኔ ገመዳ ያጠናቀረችውም አጠር ያለ ዘገባ ደርሶናል።
ሰሎሞን ክፍሌ ይሆናል የሚያቀርበው፥ ሁለቱንም ዘገባዎች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ተከሳሾች፥ ለአራተኛ ጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፣ እና በፊንፊኔ ዙሪያ የተማሪዎች ጉዳይ