በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል ያለዉን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የአፍሪቃ ሕብረት አስታወቀ።
ዋሽንግተን ዲሲ —
የአፍሪቃ ሕብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ኮሚሽነር ዶክተር አይሻ አብዱላሂ ዛሬ ለጋዜጠኞች ሲናገሩ በኦሮሚያ ክልል ስላለዉ ሁኔታ ሰፊ ዲፕሎማሳዊ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ሕብረቱ ገዢዉ መንግስት የሚፈጽማቸዉን በደሎች በተመለከት ድምጹን አያሰማም ወገንተኝነትን ያንጸባርቃል ሲሉ የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በተደጋጋሚ ይከሳሉ።
ሕብረቱ ግን በአንዳንድ ሁኔታዎች በይፋ አቋሙን የሚያንጸባርቅ ቢሆንም፣ በሌሎች ጉዳዮች ግን ከመጋረጃ ጀርባ የዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚያካሄድ ኮሚሽነርዋ ተናግረዋል።
የድምጽ ፋይሉን በመጫን ዝርዝሩን ከእስክንድር ፍሬዉ ዘገባ ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5