አምነስቲ ኢንተርናሽናል:- በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ ያለፈው የአሮፓውያኑ 2015 ዓ.ም. አሽቆልቁሏል

"መንግሥት የሚወስዳቸው የኃይል እርጃዎች ወደ አፍሪቃ ቀንድ ዘምተው እስከ ኢትዮጵያና ኤርትራ ተዳርሰዋል።" ሚሸል ካጋሪ በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር

በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ ያለፈው የአሮፓውያኑ 2015 ዓ.ም. በተለይም ለአፍሪቃ ቀንድ አገሮቹ ኢትዮጵያና ኤሪትራ ጥሩ ዘመን እንዳልነበረ፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል (Amnesty International) ገለጸ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪቃ ሕዝቦች ሽብርተኛነትን በመዋጋት የከፈሉትን መስዋዕትነት የዓለማቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ቡድን አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኤምሊ ሎብ ከአቢጃን በላከችው ዘገባ፣ ቡድኑ በዓመታዊ ሪፖርቱ፣ የመብት ጥበቃን በተመለከ በተጠቀሱት ክልሎች አንዳንድ ተጨማሪ ዕድገቶች ይስተዋላሉ ብሏል።

ሚሸል ካጋሪም በዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅት የምስራቅ አፍሪቃ፣ የአፍሪቃ ቀንድና የግሬት ሌክስ አገሮች ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር ናቸው።​

ባለፈው 2015 ዓም የነበረውንየሰብዓዊ መብት ይዞታ ሲገመግሙ፣ "በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ 2015 ዓ.ም. ጥሩ ዓመት አልነበረም።" ብለዋል።

አክለውም፣ "መንግሥት የሚወስዳቸው የኃይል እርጃዎች ወደ አፍሪቃ ቀንድ ዘምተው እስከ ኢትዮጵያና ኤርትራ ተዳርሰዋል። እና ለሰብዓዊ መብት ጥበቃም ምንም ዓይነት ከበሬታ አልነበረም። ዓለማቀፍ የሰባዊ እርዳታ አገልግሎት ህግም ወደ ሰብዓዊ ቀውስ ተለውጦ ዓለም አቀፍ የስደተኞችን ቀውስ አስከተለ። ይህ ቀውስ ባለፈው ዓመት ኤርትራን ሦስተኛዋ የስደተኞች መፍለቂያ አገር አድርጓታል። ባጠቃላይ 2015 ዓ.ም. ለሰብዓዊ መብት ጥበቃ ጥሩ ዓመት አልነበረም።" ብለዋል።

ዘገባውን ከድምጽ ፋይሉ ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በሰብዓዊ መብት ጥበቃ እረገድ ያለፈው የአሮፓውያኑ 2015 ዓ.ም. አሽቆልቁሏል