በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን እንዲለቅቁ ተቃዋሚዎች ያቀረቡትን ጥያቄ ገዢው ፓርቲ ውድቅ አደረገው


ተቃዋሚዎች ሰልፍ በሃርሃሬ ሰልፍ ወጥተው / ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/
ተቃዋሚዎች ሰልፍ በሃርሃሬ ሰልፍ ወጥተው / ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/

ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ትናንት ከብዙ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የዘጠና ሁለት ዓመቱ የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ ስልጣናቸውን እንዲለቅቁ ተቃዋሚዎች ያቀረቡትን ጥያቄ ገዢው ፓርቲ ውድቅ አደረገው። ተቃዋሚዎቹ ጥያቄውን ያቀረቡት ትናንት ከብዙ ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ የሆነውን የተቃውሞ ሰልፍ ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ
የዚምባቡዌ ፕሬዚደንት ሮበርት ሙጋቤ

የዛኑ ፒ ኤፍ ፓርቲ ቃል አቀባይ ሲሞን ካያ ሞዮ ለመንግስቱ ሄራልድ ጋዜጣ በሰጡት ቃል “ፕሬዚደንቱ ስልጣን የያዙት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ተመርጠው ነው። ተቃዋሚዎችም ተወዳድረው ማሸነፍ እንጂ ስልጣን ልቀቁ ማለት አይገባቸውም ብለዋል። ሙጋቤ እንደገና ይወዳደራሉ ተብሎ በሚጠበቅበት በሚቀጥለው እ.አ.አ 2018 ዓ.ም. ምርጫም ህዝቡ አሁንም ይቆዩልን ካለ ይመርጣቸዋል" ብለዋል ቃል አቀባዩ።

ትናንት ሃሙስ በዋና ከተማዋ በሃራሬ ከሁለት ሺህ የሚበልጡ በሞርጋን ሻንጊራይ የሚመራው የኤም ዲ ሲ (MDC) ፓርቲ ደጋፊዎች ሰልፍ አካሂደዋል። ለወትሮ በሀገሪቱ ክልክል የሆነውን የተቃዋሚ ሰልፍ እንዲበትን ፖሊስ የሚጠራ ሲሆን የትናንቱ ሰልፍም ተከልክሎ እንደነበርና ነገር ግን ዕቅግዱን ፍርድ ቤት ትናንት ውድቅ እንዳደረገው ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG