በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ


የአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን

የወልቃይት የአማራ ሕዝብ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈን ሰዎች ከያሉበት እየታሠሩ እንደሆነ የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው አስተያየት ሰጪዎ ይናገራሉ። በሰሞኑ ጉዳይ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በትናንትናው ዕለት ቃለ ምልልስ ሰጥተዋል። ጽዮን ግርማ ነች ያነጋገረቻቸው።

በጎንደር ከተማ ከሐምሌ አራት ጀምሮ በመንግሥት ኃይሎችና በሕዝቡም መካከል በተፈጠር ግጭት የሰው ሕይወት መጥፋቱ፣ ንብረት መቃጠሉን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በዛሬው ዕለት ጎንደር ከተማና በአጠቃላይ በአማራ ክልል እንየሰሞኑን በአደባባይ ሰዎች በብዛት ባይታዩም ውስጥ ውስጡን ግን ሰዎች መንቀሳቀስ እንዳቃታቸውና እየታሠሩ መሆኑን አቶ ዋሲሁን አንበሴ ይናገራሉ።

አዲስ አበባ የሚገኙና የወልቃይት ተወላጅ መሆናቸውን የገለጹት አቶ ሃይሉ አንበሴ በበኩላቸው አዲስ አበባ ያሉ የወልቃይት ተወላጆች ዛሬ መታሰራቸውን ይገልጻሉ።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የተፈጠረውን ሁኔታ ለማብረድ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ነገር ተረጋግቶ ነገሮች ወደነበሩበት እየተመለሱ መሆኑን ተናግረዋል።

ጽዮን ግርማ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አነጋግራቸዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

ከአማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ
please wait

No media source currently available

0:00 0:27:43 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አስተያየቶችን ይዩ (52)

XS
SM
MD
LG