በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ - አፍሪካ ጉባዔ እና የዩክሬኑ ጦርነት


የሩሲያ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ
የሩሲያ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ
የዩክሬን ወታደሮች በዶኔትስክ ግዛት የምትገኘውን ደቡብ ምስራቃዊቱን የስታራማዮርስክን መንደር መልሰው ተቆጣጠሩ። ርምጃው ዩክሬይን በሩሲያ በተያዙት የይክሬን ደቡብ ምስራቃዊ የአገሪቱ አካባቢዎች የጀመረችው የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴ አካል መሆኑ ተነግሯል።
በተያያዘ ዜና አብራምስ የተባሉት የዩናይትድ ስቴትሱ ታንኮች የፊታችን መስከረም ዩክሬን ሊደርሱ እንደሚችሉ ተገልጿል። በተያያዘ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ በቅርቡ በሩሲያ የአየር ጥቃት የተጎዳውን ታሪካዊውን የኦዴሳ ካቴድራል መጎብኘታቸው ተዘግቧል።
በሌላ በኩል ሩሲያ ከጥቁር ባህሩ ስምምነት በወጣች ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሩሲያ እና የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ ትላንት ሐሙስ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ተጀምሯል።

በጉባዔው ላይ የተገኙት 17 የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መሆናቸው ተመልክቷል። በመጀመሪያው የሩስያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ አርባ ሶስት የአፍሪካ መሪዎች መገኘታቸው ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG