በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲንና ዐቢይ ሴ’ንት ፒተርስበርግ ላይ ተገናኝተው ተወያዩ


ፑቲንና ዐቢይ ሴ’ንት ፒተርስበርግ ላይ ተገናኝተው ተወያዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:54 0:00

ፑቲንና ዐቢይ ሴ’ንት ፒተርስበርግ ላይ ተገናኝተው ተወያዩ

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በሴንት ፒተርስበርግ ላይ ተገናኝተው ተወያዩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ በነገው ዕለት በሚጀመረው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፣ በዛሬው ዕለት ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ እንደገቡ ሲታወቅ፣ በከተማዋ፣ ከፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ተገናኝተው እንደተወያዩ፣ የአሶሺዬትድ ፕሬስ ዘገባ አመልክቷል።

“ጉባኤው፣ 1ነጥብ3 ቢሊዮን ሕዝብ ለሚኖርባትና በዓለም መድረክ ላይ አቋሟን ይበልጥ በማንጸባረቅ ላይ ከምትገኘው የአፍሪካ አህጉር ጋራ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የሚረዳ ከፍተኛ ኹነት ነው፤” ሲሉ፣ ቭላድሚር ፑቲን እንደተናገሩ ዘገባው አመልክቷል።

“ሩሲያ እና ኢትዮጵያ፣ በወቅታዊ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አቋም ይጋራሉ፤” ሲሉ፣ አክለዋል ፑቲን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በበኩላቸው፣ ሁለቱ ሀገራት፣ ረጅም ታሪክ እንዳላቸው አውስተው፣ በቴክኖሎጂ፣ በሳይበርሴኩሪቲ፣ በኢኮኖሚ እና በንግድ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ መናገራቸው ተጠቁሟል።

ነገ የሚከፈተው፣ የሁለት ቀናት ጉባኤ፣ እ.አ.አ በ2019 ከተደረገው የመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የቀጠለው ሁለተኛው ጉባኤ ነው።

በጉባኤው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ከተጠበቁት 43 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ፣ የሚሳተፉት 17 ብቻ ናቸው፤ ተብሏል። የቁጥሩ መቀነስ፣ “የምዕራቡ ዓለም፣ የአፍሪካ ሀገራት በጉባኤው ላይ እንዳይሳተፉ በመወትወቱ ምክንያት የመጣ ነው፤” ሲል፣ ክሬምሊን ክሥ አሰምቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG