በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተፎካካሪዎች ውድድሩን ወደ ኒው ሃምፕሸር አዙረዋል


የኦሃዮ ሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ጆን ካሲች በኒው ሃምፕሸር
የኦሃዮ ሪፐብሊካን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ጆን ካሲች በኒው ሃምፕሸር

ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የፓርቲዎቻቸው እጩ በመወዳደር ላይ ያሉት ተፎካካሪዎች ውድድሩን ወደ ኒው ሃምፕሸር አዙረዋል።

በሚቀጥለው ዓመት በሕዳር ወር ለሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የፓርቲዎቻቸው እጩ ሆኖ ለመቅረብ በመወዳደር ላይ ያሉት ተፎካካሪዎች የትላንት በስቲያውን የግዛቶች ውድድር ያስተናገደችውን የአየዋውን (Iowa) ምርጫው ውድድር መጠናቀቅ ተከትሎ ፊታቸውን ወደ ሰሜን ምሥራቋ ኒው ሃምፕሸር አዙረዋል።

ተፎካካሪቹን የፊታችን ማክሰኞ ከሚያካሂዱትና ድምጽ ሠጪዎች ምርጫቸውን ለይተው ከማስታወቃቸው አስቀድሞ ሌላ ዙር ክርክር ያደርጋሉ።

የዲሞክራቱ ፓርቲ ተወዳዳሪዎች የቀድሞዋ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትርሴናተር ሂላሪ ክሊንተን በዛሬው ምሽት ከተቀናቃኛቸው ሴናተር በርኒ ሳንደርስጋር ታዳሚ በተሰበሰበት አዳራሽ ለምን መመረጥ እንዳለባቸው ለመራጩ ኅዝቡለማሳየት ይጥራሉ።

በነገው ምሽት ሌላ መደበኛ አቀራረብ የተከተለ ክርክርተይዟል። የሪፐብሊካን ተፎካካሪዎች በበኩላቸው ቅዳሜ ይከራከራሉ።

XS
SM
MD
LG