በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞቱት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚተካ ሰው የመሰየሙ ሂደት የፖለቲካ ጦርነት ከፈተ


ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አንቶኒን ስካልያ (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)
ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አንቶኒን ስካልያ (አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

ስካልያን በሚተኩት እጩ ላይ የፖለቲካ ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው በዋይት ሃውስ ቤተ መንግስትና በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት መካከል ነው። ስካልያን በሚተኩት ሰው ምርጫ ላይ የፖለቲካ ጦርነቱ እየተካሄደ ያለው በዋይት ሃውስ ቤተ መንግስትና በሕግ መወሰኛው ምክር ቤት መካከል ነው።

በዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለረዥም ዓመታት በዳኝነት በማገልገል የታወቁት ወግ አጥባቂ ዳኛ አንቶኒን ስካልያ ባለፈው ቅዳሜ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ስካልያ በ 79 ዓመታቸው ድንገት በተኙበት ያረፉት ቴክሳስ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ነው።

ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ለስካልያ ያላቸውን ክብር ከገለጹ በሁዋላ፥ ሕገ-መንግሥታዊ ሥልጣናቸውን በመጠቀም የቀድሞውን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚተካ እጩ ባጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚያሳውቁ ገልጸዋል።

የሪፐብሊካን ፓርቲው መሪዎች ግን፥ አዲሱን እጩ መምረጥ ያለበት ቀጣዩ ያሜሪካ ፕሬዘዳንት መሆን አለበት ሲሉ ተቃውመዋል። ዘጋቢዎቻችን ያጠናቀሯቸው በርካታ ሪፖርቶች አሉ።

ሰሎሞን ክፍሌ ለቀጣዩ ዲሞክራሲ በተግባር ፕሮግራሙ እንደሚከተለው አሰናድቶታል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

በሞቱት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የሚተካ ሰው የመሰየሙ ሂደት የፖለቲካ ጦርነት ከፈተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:29 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG