በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኩባው አቻቸው ራውል ካስትሮ ጋር እየተወያዩ ነው


ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኩባው አቻቸው ራውል ካስትሮ ጋር እየተወያዩ
ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኩባው አቻቸው ራውል ካስትሮ ጋር እየተወያዩ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ትናንት እሁድ ኩባ ገብተዋል። ለግማሽ ምዕተ ዓመት የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት የባላንጣ ግንኙነት ምዕራፍ ይዘጋል የተባለውን ውይይትም በዛሬው ዕለት ከኩባ መሪዎች ጋር በማድረግ ላይ ናቸው።

ከ90 ዓመታት በኋላ ኩባን የጎበኙ የመጀመሪያው አሜሪካዊ መሪ ኾነዋል ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ። የቀዝቃዛውን ጦርነት ጨምሮ ከግማሽ ምእት ዓመት በላይ ሆድና ጀርባ ኾነው የቆዩት የሁለቱን ሀገሮች የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ የሚያድስ ውይይት በዛሬው ዕለት ሲካሄድ ውሏል። ፕሬዚደንት ኦባማ ከኩባው አቻቸው ራውል ካስትሮ ጋር የሁለቱን ሀገሮች ግንኙነትና የሰብዓዊ መብት ይዞታ በማሻሻል ዙሪያ ይነጋገራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

እነዚህ ውይይቶች በኩባና ዩናይትድ ስቴይትስ መካከል ከ50 ዓመታት በላይ ይዘለቀው የሻከረ ግንኙነት እንደገና እንዲሻሻል በር ይከፍታሉ ተብሎላቸዋል።

ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ወደ ኩባ ያመሩት ቤተሰቦቻቸውን፣ የሕዝብ ተወካዮችን፣ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ ባለስልጣናትንና ኩባዊ አሜሪካዊ የንግድ ድርጅት መሪዎችን ያካተተ ቡድን ይዘው ነው። በኩባ የሚያደርጓቸው ውይይቶች በውጭ ግንኙነት፣ በንግድ ግንኙነቶችና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ነገም ይቀጥላል።

የቬኦኤው ዘጋቢያችን ሪቻርድ ግሪን ከሃቫና ያጠናቀረውን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያዳምጡ፡፡

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከኩባው አቻቸው ራውል ካስትሮ ጋር እየተወያዩ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ፕሬዚዳንት ኦባማ ከ 90 ዓመታት በኋላ ኩባን ለመጀመሪያ ጊዜ እየጎበኙ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:08 0:00

XS
SM
MD
LG