በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ የኦሮሞ ብሄረሰብ ብሶትን በተመለከተ ትርጉም ሰጪ ድርድር እንዲካሄድ ጥሪ አቀረበች


ፋይል ፎቶ - ቃል-አቀባይ ጆን ኪርቢ እአአ 2014 (አሶሽየትድ ፕረስ/AP)
ፋይል ፎቶ - ቃል-አቀባይ ጆን ኪርቢ እአአ 2014 (አሶሽየትድ ፕረስ/AP)

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እየያዙ የማሠር እርምጃዎች በኦሮሚያ የቀረቡ ተገቢ የፖለቲካ ብሶቶችን በምክክር ለመፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ከባድ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የኦሮሞ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን ማሠር ጨምሮ ሃሳብን በነፃ የመግለጽ መብቶችን ማፈን መቀጠሉ ይበልጥ እያሳሰባት መጥቷል። እነኚህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችን እየያዙ የማሠር እርምጃዎች በኦሮሚያ የቀረቡ ተገቢ የፖለቲካ ብሶቶችን በምክክር ለመፍታት በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ከባድ ተፅዕኖ ይኖራቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በወሰዳቸው እርምጃዎች ከተጎዱት ማህበረሰቦች ጋር በይፋ ለመወያየት ባለፈው ታህሳስ የገባውን ቃል እንደግፋለን። እነዚህ ውይይቶች ትርጉም ሰጪ እንዲሆኑ ደግሞ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ መቻል አለባቸው።

የኢትዮጵያ መንግሥት፥ በነጻ የመሰብሰብ፥ የመጻፍ፥ እና ዜጎች ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶቻቸውን ማክበርን ጨምሮ ተቃውሞን ከማፈን ተግባሩ እንዲታቀብ ያቀረብነውን ጥሪ ዳግም እናስተጋባለን።

እነዚህን መብቶቻቸውን ለመጠቀም ሲሞክሩ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና ጋዜጠኞች ያሉትን ጨምሮ የታሠሩት ሁሉ እንዲፈቱ ጥሪ እናቀርባለን።

XS
SM
MD
LG