ካምፓላ —
በዑጋንዳው ፕሬዝዳንታዊ የቃለ መሃላ ሥነ ሥርዓት የታደሙ የዩናይትድ ስቴትስ፥ የካናዳና የአውሮፓ ሕብረት ልዑካን በጦር ወንጀል የሚፈለጉት የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በሥነ ሥርዓቱ መገኘታቸውን በዝምታ ተቃውሞ ገለጡ።
ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር ከቀትር በኃላ ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሞሴቨኒ ቃለ መሃላ በፈጸሙበት ሥነ ሥርዓት ከተገኙ በኃላ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ምዕራባውያኑን ልዑካን ለዝምታ ተቃውሞው ያነሳሳው በጅምላ ጭፍጨፋና በጦር ወንጀለኝነት ተጠርጥረው ሄግ በሚገኘው ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ችሎት፤ በእንግሊዝኛው ምሕጻረ ቃል ICC የሚፈለጉት የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ኦማር አልበሽር በሥነ ሥርዓቱ በመገኘታቸውና የዑጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮወሪ ሞሴቬኒ ችሎቱን በማሳነስ የሰጡት አስተያየት ነው።
ሊዛቤት ፑላት ከካምፓላ ያጠናቀረችውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።