በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምርጫው ቀዝቃዛ አይደለም - ገብሩ አሥራት (አረና)


"ዓረና/መድረክ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም የተሻለ ድርጅት ነው" ብለዋል አቶ ገብሩ አሥራት፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:15:19 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

"ዓረና/መድረክ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚጠቅም የተሻለ ድርጅት ነው" ብለዋል አቶ ገብሩ አሥራት፡፡

የዘንድሮ የምርጫ ሂደት ቀዝቅዟል የሚል አስተያየት መኖሩንና አቶ ገብሩ ሁኔታውን እንዴት እንደሚገመግሙት ተጠይቀዋል፡፡

መድረክ የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በጣም አመርቂና ሰፊ ናቸው የሚሉት አቶ ገብሩ አሥራት ምርጫው ቀዝቃዛ ነው እንደማይሉ ተናግረዋል፡፡

መድረክ በኦሮሚያ በሚያደርጋቸው የቅስቀሣ ስብሰባዎች እስከ ሰላሣ ሺህ ሰው እየተገኘ መሆኑን የገለፁት አቶ ገብሩ በደቡብም ተመሣሣይ ሁኔታ እየታየ መሆኑን፤ በትግራይም በተለያዩ አካባቢዎች ቅስቀሣዎቻቸውን እያካሄድ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

በሕዝቡ በኩልም የሚታየው ቀደም ሲል ከነበረው የበለጠ ተነሣሽነት እንደሆነም አቶ ገብሩ አክለው ጠቁመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG