ዋሺንግተን ዲሲ - መቀሌ —
መቀሌ ላይ ለሁለት ቀናት ታስረው የነበሩት የተቃውሚው አረና ትግራይ መሪ ዛሬ ረቡዕ ጥር 20/2007 ዓ.ም ተፈትተዋል፡፡
የአረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ለሉዓላዊነት ሊቀመንበር አቶ ብርሃኑ በርኸ ከከትናንት በስተያ ሰኞ ጥር 18/2007 ዓ.ም የታሠሩት ወንጀል ተፈፅሞበታል ተብሎ በሚጠረጠር ቤት ውስጥ በመገኘታቸው፣ በወንጀል አድራጎት ትብብርና “ፖሊስ ተሣድበሃል” በሚሉ ምክንያቶች እንደነበር የፓርቲው የቀድሞ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አሥራት ትናንት - ማክሰኞ ለቪኦኤ በስልክ ገልፀው ነበር፡፡
አቶ ብርሃኑ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል “የታሠርኩት በፖለቲካ ማዋከብ ነው፤ የተፈታሁትም በፖለቲካ ነው” ብለዋል፡፡