በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋናው የሦርያ ተቃዋሚ ቡድን በሰላም ድርድር ለመካፈል ፍላጎት እንዳለው ፍንጭ ማሳየቱ ተገለጸ


የአደራዳሪው ከፍተኛ ኰሚቴ ቃል-አቀባይ ሬድ ናሳን አጋ ሲናገሩ፣ ተወካዮች የፊታችን ዐርብ ጄኔቫ ለመግባት ማቀዳቸውን ጠቅሰዋል።

ዋናው የሦርያ ተቃዋሚ ቡድን፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሚመራውና በዚህ ሳምንት ማብቂያ ገደማ በሚጀመረው የሰላም ድርድር የመካፈል ፍላጎት እንዳለው ዛሬ ሰኞ ፍንጭ ማሳየቱ ተገለጸ።

የአደራዳሪው ከፍተኛ ኰሚቴ ቃል-አቀባይ ሬድ ናሳን አጋ ሲናገሩ፣ ተወካዮች የፊታችን ዐርብ ጄኔቫ ለመግባት ማቀዳቸውን ጠቅሰዋል።

ቃል-አቀባዩ አክለውም፣ እ.አ.አ. ባለፈው የካቲት 27 ቀን ሥራ ላይ የዋለው የተኩስ አቁም ስምምነት እየተጣሰ ለመሆኑ ዘገባዎች እንደደረሷቸውና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦቱም እያሽቆለቆለ እንደሆነ አመልክተዋል።

የሩስያው ውጩ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭና የዩናይትድ ስቴትስ አቻቸው ጆን ኬሪ ትናንት እሑድ በቴሌፎን ሲነጋገሩ፣ አዲስ የሚጀመረው የሰላም ድርድር መዘግየት እንደሌለበት ተስማምተዋል። ጆን ኬሪ ከዚህ በፊት የሰጡትን መግለጫ ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በሶርያ ላይ ያደረጉት ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:43 0:00

XS
SM
MD
LG