ዋሺንግተን ዲሲ —
የኢራን ፕሬዚዳንት ሃሰን ሩሃኒ ሁሉም ባለሥልጣኖች ሊነቀፉ ይችላሉ፤ በሀገሪቱ ተቃውሞ የሚያካሄዱትን ሰዎች ያሳዘነው የኢኮኖሚ ሁኔታ ብቻ አይደለም ብለዋል።
በማኅበራዊ ሚድያ ላይ የተጣለው ዕገዳ እንዲነሳም ሩሃኒ ጥሪ አድረገዋል።
ለሁለት ሳምንታት ከሚጠጋ ጊዜ በፊት አንስቶ ኢራን ውስጥ ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ መንግሥት መልዕክት በሚተላለፍባቸው አፖች ላይ ቴሌግራምና ኢንስቶግራም ጭምር ዕገዳ ጥሏል። በኢንስቶግራም ላይ የተደረገው ዕገዳ ትላንት ተነስቷል። ቴሌግራም ግን እንደታገደ ነው።
እአአ ከ2009 አንስቶ ኢራን ውስጥ ይህን ያክል ትልቅ ፀረ መንግሥት ተቃውሞ አልታካሄደም። ተቃዋሚዎቹ የሥራ አጥነት ችግርና የምግብ ዋጋ መናር ጥያቄ እያነሱ ናቸው። በመንግሥት ለውጥ እንዲደረግም እየጠየቁ ናቸው።
የኢራን ምክትል የፍርድ ቤት ኃላፊ ሐሚድ ሻህሪያሪ የወቅቱ ተቃውሞ መሪዎች ሁሉ ታሥረዋል። ከባድ ቅጣት ይጠብቃዋል ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል። እስካሁን ባለው ጊዜ ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች ተገድለው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታሥረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ