በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራን ፀረ መንግሥት ኃይሎችና የመንግሥቱ ደጋፊዎች የውጪ ጣልቃ ገብነትን አወገዙ


ኢራን ውስጥ ፀረ መንግሥት ኃይሎችና የመንግሥቱ ደጋፊዎች፤ የውጪ ጣልቃ ገብነትን በጋራ አወገዙ።

ኢራን ውስጥ ፀረ መንግሥት ኃይሎችና የመንግሥቱ ደጋፊዎች፤ የውጪ ጣልቃ ገብነትን በጋራ አወገዙ።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራን ሕዝብ እንቅስቃሴ ድጋፍ እንደምታደርግ ስትገልፅ፣ በተመድ የኢራን መልዕክተኛ በበኩላቸው ይህ ማለት “እሳት ላይ ቤንዚን መጨመር ነው” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስን ጣልቃ ገብነት አወገዙ።

ኢራን ውስጥ ፀረ መንግሥት እንቅስቃሴ የተጀመረው ባለፈው ሳምንት መሆኑ ይታወሳል። በዚህ፣ የመንግሥት ለውጥ እንዲደረግና የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እንዲሻሻል በሚጠይቀው ተቃውሞ፣ ቢያንስ ሃያ አንድ ሰዎች ሞተዋል፣ ባለሥልጣናትም በመቶዎች የሚቆጠሩትን አስረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለኢራን ተቃዋሚዎች የድጋፍ መልዕክት ማስተላለፋቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG