በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የማሕበረሰብ ድረገጾች ሚና በኦሮሚያ ተቃውሞ


ጃዋር ሲራጅ መሀመድ (Jawar Mohammed) /ከፌስ ቡክ የተገኘ ፎቶ/
ጃዋር ሲራጅ መሀመድ (Jawar Mohammed) /ከፌስ ቡክ የተገኘ ፎቶ/

በዛሬው ዝግጅት የማሕበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን በኦሮሚያ የተቃውሞ ሰልፎች ያለውን ሚና እንገመግማለን። እነዚህን ሁኔታዎች በማሕበረሰብ ድረገጽ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለውና ከ435 ሽህ በላይ ተከታዮች ያሉት ጃዋር ሲራጅ መሀመድ ጋር ከተደረገው ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።

በህዳር ወር የመጀመሪያ ሳምንት፤ በኦሮሚያ ጊንጪ ከተማ አካባቢ የሚገኝ ደን ለአንድ የግል ኢንቨስተር መሸጡና የአንድ ትምህርት ቤት እግር ኳስ መጫወቻ ሜዳም እንዲሁ “ለልማት” በሚል ተሰጠ ሲሉ የከተማዋ ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጡ።

የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃንም በዚያን ቀን #OromoProtests በሚል በብዛት በፌስቡክና በትዊተር መልእክቶች፣ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች በስፋት መሰራጨት ጀመሩ።

Keyhole Hashtag Tracking on #OromoProtests
Keyhole Hashtag Tracking on #OromoProtests

በማህበረሰብ መገናኛ ብዙሃን ከሚሰራጩት መልእክቶች፤ ፎቶዎችና ቪዲዮዎች መካከል የሚበዙት ከዩናይትድ ስቴይትስና ከአውሮፓ የወጡ ናቸው፤ የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንቅስቃሴን የሚከታተለው “Keyhole Hashtag Tracking” መረጃ መሰረት።

የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንቅስቃሴን የሚከታተለው “Keyhole Hashtag Tracking” #OromoProtests
የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን እንቅስቃሴን የሚከታተለው “Keyhole Hashtag Tracking” #OromoProtests

41 ከመቶ ከዩናይትድ ስቴይትስ፤ 9ከመቶ ከካናዳ፤ ከአውሮፓ ደግሞ ወደ 25 ከመቶ የሚጠጋ፤ ሲሆን ከኢትዮጵያ ደግሞ 17 ከመቶ መረጃዎች መጥተዋል።

በዛሬው ዝግጅት የማህበረሰብ የመገናኛ ብዙሃን በኦሮሚያ የተቃውሞ ሰልፎች ያለውን ሚና እንገመግማለን።

እነዚህን ሁኔታዎች በማህበረሰብ ድረገጽ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለውና ከ435 ሽህ በላይ ተከታዮች ያሉት ጃዋር ሲራጅ መሀመድ ጋር ከተደረገው ቃለ-ምልልስ ያዳምጡ።

የማሕበረሰብ ድረገጾች ሚና በኦሮሚያ ተቃውሞ
please wait

No media source currently available

0:00 0:19:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG