የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ እየሩሳሌምን በእስራኤል ዋና ከተማነት ዕውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ፍልስጤማውያን “የቁጣ ቀን” ብለው በጠሩት ዓመፁ ጋዛ ላይ የእስራኤል ወታደሮች አንድ ፍልስጥጤማዊ ገድለዋል።
ማህሙድ አል ማስሪ የተባለው የሠላሳ ዓመት ሰው እስራኤልና ጋዛ ድንበር ላይ መገደሉን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የእስራኤል የጦር ኃይልም
"ዋናዎቹ የብጥብጥ ቀስቃሾች .." ሲል የገለፃቸውን ሁለት ሰዎች በጥይት መተናል ሲል አረጋግጧል።
በመካከለኛው ምሥራቅ እና የሚበዛው ህዝባቸው የእስልማና ሃይማኖት ተከታዮች በሆኑ ሀገሮች ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች እይተካሄዱ ናቸው።
ኢራቅ፣ ዮርዳኖስ፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታን፣ ሌባኖስ፣ ማሌዥያን፣ ኢንዶኔዥያ ውስጥ ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል።
ሃማስ በእስራኤል ላይ ዓመፅ እንድካሂድ ጥሪ አሰምቷል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት የወሰዱት አቋም እስራኤል ሰላሙዋን እንድታገኝ ላለፉት በርካታ ዓመታት ከተካሄዱት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች የራቀ ነው።
በሠላም ፍለጋው ጥረት አንደኛው ትልቁ መሰናክል ሆኖ የእየሩሳሌም ጉዳይ መፍትኄው መፈለግ ያለበት በሰላም ሂደቱ ድርድር መሆን እንዳለበት ታምኖበት ቆይቷል።
ትናንት ዋይት ኃውስ ሲናገር ፕሬዚደንቱ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ወደእየሩሳሌም እንደሚዛወር መናገራቸው አስተዳደሩ ከመካከለኛው ምሥራቅ የሰላም ድርድር ወጣ ማለት አይደለም ብሏል።
እስካሁን ዩናይትድ ስቴትስትን ተከትሎ ኤምባሲዬን ከቴል አቪቭ ወደእየሩስሌም አዛውራለሁ ያለ ሀገር የለም፡፡
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ