በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ “እየሩሳሌም የእሥራኤል መዲና ናት” ዕውቅና፣ የአረብ ሀገራትና የሙስሊሙ ዓለም

Palestinian militants of PFLP burn representations of an Israeli flag and a U.S. flag during a protest..
Palestinian militants of PFLP burn representations of an Israeli flag and a U.S. flag during a protest..

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “እየሩሳሌም የእሥኤራል መዲና ናት” የሚል ዕውቅና በሰጡ ማግሥት በምዕራብ ዳርችና በጋዛ ለተቃውሞ በወጡ ፍሊሥጤማውያንና በእሥራኤል ወታደሮች መካከል ግጭት ተነስቷል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ “እየሩሳሌም የእሥኤራል መዲና ናት” የሚል ዕውቅና በሰጡ ማግሥት በምዕራብ ዳርችና በጋዛ ለተቃውሞ በወጡ ፍሊሥጤማውያንና በእሥራኤል ወታደሮች መካከል ግጭት ተነስቷል።

በምዕራብ ዳርቻ ፍሊስጤማውያን በእሥራኤል ወታደሮች ላይ ድንጋይ ወርውረዋል። የፍሊስጤማውያን መንግሥት ባለበት ራማላ ደግሞ የመኪና ጎማዎችን በእሣት አጋይተዋል፣ ከተማይቱ ጥቅጥቅ ባለ ጥቁር ጭስ እንደተሞላች ተዘግቧል። በግጭቱ ብዙ ሰዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ቤትልሔም ውስጥ ወታደሮች በተቃዋሚዎቹ ላይ ዕምባ አስመጪ ጋዝ ተኩሰዋል፣ ከባድ የውሃ ግፊትም ረጭተዋል።

ትረምፕ “እየሩሳሌም የእሥራኤል መዲና ናት” ዕውቅና፣ የአረብ ሀገራትና የሙስሊሙ ዓለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:56 0:00

በጋዛ የወጡት ተቃዋሚዎች በበኩላቸው የትረምፕንና የእሥራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኒታንያሁ ምሥሎችን በእሣት አቃጥለዋል። የዩናይትድ ስቴትስንና የእሥራኤል ባንዴራዎችንም አቃጥለዋል።

እሥራኤል በምዕራብ ዳርቻ፣ በምሥራቅ እየሩሣሌምና በጋዛ ድንበር የፀጥታ ኃይሎችን አጠናክራለች።

ትረምፕ እየሩሳሌም የእሥራኤል መዲና ናት የሚል ዕውቅና መስጠታቸው የአረብ ሀገሮችንና የሙስሊሙን ዓለም አስቆጥቷል፣ የዩናይትድ ስቴትስ አጋር ሀገሮችንም አስደምሟል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG