በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ሸዋ ዞን 14 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ


በሰሜን ሸዋ ዞን 14 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

በሰሜን ሸዋ ዞን 14 ሲቪሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ

በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ህዴቡ አቦቴ ወረዳ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ቢያንስ 14 ሲቪሎች እንደተገደሉ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

በጉዳዩ ላይ፣ ከህዳቡ አቦቴ ወረዳ አስተዳዳሪ፣ ከኤጄሬ ከተማ፣ ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እና ከኦሮሚያ ጸጥታ እና አስተዳደር ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

ላለፉት ሁለት ቀናት በተካሔደው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ መንግሥት አሁንም ለሰላም ውይይት ዝግጁ መኾኑን ገልጸው፣ ታጥቆ በሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ላይ እየተወሰደ ያለው ርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG