በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መንግሥት በዐማራ ክልል “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” ቢልም የጸጥታ ችግሩ እንደተባባሰ ነዋሪዎች ገለጹ


መንግሥት በዐማራ ክልል “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” ቢልም የጸጥታ ችግሩ እንደተባባሰ ነዋሪዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:03 0:00

መንግሥት በዐማራ ክልል “አንጻራዊ ሰላም ሰፍኗል” ቢልም የጸጥታ ችግሩ እንደተባባሰ ነዋሪዎች ገለጹ

በዐማራ ክልል አንጻራዊ ሰላም እንደሰፈነ፣ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት አካላት ሰሞኑን ቢገልጹም፣ የጸጥታ ችግሩ እየተባባሰና የከፋ ጉዳትም እየደረሰ እንደኾነ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ነዋሪዎች፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

መንግሥት፣ በክልሉ የተሟላ አንጻራዊ ሰላም እንደሰፈነ መግለጹን ተከትሎ፣ የሰዓት እላፊን ጨምሮ የተለያዩ ማስተካከያዎች ማድረጉን፣ የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ፣ ትላንት እሑድ አስታውቋል፡፡

የሰዓት ገደብ ማሻሻሻያው በዋናነት፡- በጎንደር፣ በደብረ ብርሃንና በባሕር ዳር ከተሞች ላይ እንደሚተገበር ሲጠቀስ፤ እንደየአካባቢዎቹ የሰላም ይዞታም፣ በየቀጣናዎቹ ባሉ ኮማንድ ፖስቶች በቀጣይ የሚደረጉት ማሻሻያዎች እንደሚገለጹ ተጠቁሟል፡፡

ከዚኽ የክልሉ እና የፌዴራል መንግሥት መግለጫ በተፃራሪ፣ የጸጥታ ችግሩ እንደተባባሰና ዛሬም ቀጥሎ እንደዋለ በገለጹት ግጭት፣ የደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎች እየተቃጠሉ እንደኾነ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ነዋሪዎች፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው ጥቅምት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የበረኸት ወረዳ ከተማ በኾነው መተህብላ ላይ በደረሰውና በድሮን እንደተፈጸመ በገለጹት ከባድ ፍንዳታ፣ በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት መድረሱን፣ የከተማው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ፣ እስከ አሁን ከመንግሥት የተሰጠ ማረጋገጫም ኾነ ማስተባበያ የለም፡፡

በዚያ “ከባድ ፍንዳታ” ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ወደ ከተማው ጤና ጣቢያ ከመጡት ውስጥ፣ የአምስት ሰዎች ሕይወት እንዳለፈ በተቋሙ የሚያገለግሉ አንድ የጤና ባለሞያ ለአሜሪካ ድምፅ አረጋግጠዋል፡፡ ነዋሪዎች ግን፣ “እጅግ ብዙ ነው፤” ሲሉ የጉዳቱን አስከፊነት ገልጸዋል፡፡

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG