በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ


ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:43 0:00

የኢጣልያው የወደብ ዘብ ጠባቂም በሽህዎች የሚቆጠሩትን ማዳኑ ታውቋል። በሕይወት የተረፉት እንደሚናገሩት ህገ-ወጥ አሻጋሪዎቹ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ፈጽመውባቸዋል።

አየሩ የሞቀ፣ ባሕሩም ፀጥ ያለ ቢሆንም ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ።

የኢጣልያው የወደብ ዘብ ጠባቂም በሽህዎች የሚቆጠሩትን ማዳኑ ታውቋል። በሕይወት የተረፉት እንደሚናገሩት ህገ-ወጥ አሻጋሪዎቹ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ ፈጽመውባቸዋል።

በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ከሞት የተረፉ ፍልሰተኞችን የጫነው የኢጣልያ ባሕር ኃይል መርከብ፣ ትናንት እሑድ ነው ረጂዮ ካላብሪያ ወደብ ላይ የደረሰው።

የተረፉ ፍልሰተኞችን የጫነው የኢጣልያ ባሕር ኃይል መርከብ በረጂዮ ካላብሪያ ወደብ ላይ
የተረፉ ፍልሰተኞችን የጫነው የኢጣልያ ባሕር ኃይል መርከብ በረጂዮ ካላብሪያ ወደብ ላይ

የሜዲትሬንያንን ባሕር ለማቋረጥ ሲሞክሩ ሕይወታቸውን ያጡ የ45 ሰዎች አስከሬንም አብሮ ተጭኗል። ከሞት የተረፉትና ብዙዎቹ ነጭ የለበሱት ፍልሰተኞች ከመርከቧ ሲወርዱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ሠራተኞች ተቀብለዋቸዋል።

ሉቴነንት ማርዮ የኢጣልያ ባሕር ኃይል ኮማንደር ናቸው። ስደተኞቹን የተቀበሏቸው ሠራተኞች እንዲህ በማለት ሃሳባቸውን ገልጸዋል "መርከቡ ላይ የነበሩ የባሕር ኃይሉ ዶክተሮች ምስጋና ይድረሳቸውና ለብዙዎቹ ፍልሰተኞች፣ የሕክምና እርዳታ ልንሰጣቸው ሞክረናል። በአጋው ልብሶቻቸውን ላጡትም የሚለብሱትን አዘጋጅተናል። ትኩስ ምግብም እንዲሁ።" ብለዋል።

የአሜሪካ ድምጽ የፍልሰተኞችና ስደተኞች ጉዞን በዝርዝር የሚዳስስ "ከርታታ ሥውሩ የአፍሪካ ዳያስፖራ" የተሰኘ ዘገባ አዘጋጅቷል። ፋይሉን በመጫን ይጎብኙ።

ኢጣልያ ላደረገችው ሕይወት-አድን ሥራ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስጋና አቅርቧል። ከተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የስደተኞች ኰሚሽን፣ የጄኔቭ ቢሮ፣ ዊልያም ስፒንድለር "የኢጣልያ ባሕር ኃይል እጅግ አስደናቂ ተግባር ፈጽሟል። እስካሁን በዚህ ሳምንት ብቻ ከ14,000 በላይ ሕይወት አድነዋል። አለመታደል ሆኖ ግን፣ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። በተለያዩ ሦስት የመርከብ አደጋዎች፣ ወደ 700 ያህል ሕይወት እንደጠፋም እንገምታለን። " ብለዋል።

የነዚህ አደጋዎች ሰለባ የሆኑት ብዙዎቹ፣ ከሰሓራ በታች ካሉ የአፍሪቃ አገሮች መሆናቸውን ባለሥልጣናት ይናገራሉ። በሕይወት የተረፉት እንደሚናገሩት፣ ህገ-ወጥ አሻጋሪዎቹ፣ የማናቸውንም ተሳፋሪዎች ሕይወት ለማዳን ጥረት አላደረጉም።

ጂዮቫምዲ በነዲክት የኢጣልያ (Save the Children) ሠራተኛ ናቸው። የፍልሰተኞቹን ጉዞ ሲገልጹ "ባለፈው ረቡዕ ማታ ከሊብያ ከተነሱት ሦስት ያህል የአሳ-አጥማጅ ጀልባዎች ውስጥ አንዱ ወደ 500 ሰዎችን ጭኖ፣ ሌላውን ወደ 400 ሰዎች የጫነውን አነስተኛ ጀልባ ይጎትታል። በማግስቱ ሐሙስ ጠዋት፣ ይጎተት የነበረው አነስተኛ ጀልባ ውኃ ሲሞላው አንዳንዶቹ ወደ ትልቁ ጀልባ ለመሻገር ሞከሩ። በመሀል መገመዱ ሲበጠስ፣ ትንሹ ጀልባ ሰጠመ።" ብለዋል።

ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ
ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ

የኢጣልያ ባለሥልጣናት 4 ተጠርጣሪ ህገ-ወጥ ነጋዴዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል። ከነዚህ አንዱ፣ ከምትጎተተው ጀልባ ገመዱ እንዲበጠስ ያደረገና ጎታቿን ጀልባ ይዞ የነበረ ሱዳናዊ መሆኑም ተገልጧል።

የተ.መ.ድ. የስደተኞች መሥርያ ቤት እንዳስታወቀው፣ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 200,000 ሰዎች ሜዲትሬንያን ባሕርን ያቋረጡ ሲሆን፣ አሁን በመጨረሻ ከደረሰው አደጋ አስቀድሞ፣ ወደ 1,700 የሚሆኑት ወይ ሞተዋል አልያም የት እንደደረሱ አልታወቀም።

ዛልቲካ ሆኬ የደረሰንን ዘገባ አዲሱ አበበ አቅርቦታል።

ከ700 በላይ ፍልሰተኞች ሜዲትሬንያንን ለማቋረጥ ሲሞከሩ መስጠማቸው ተነገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:14 0:00

XS
SM
MD
LG